ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
የንጉሠ ነገሥቱ ታሪክ / From Wikipedia, the free encyclopedia
ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ የኢትዮጵያ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ነበሩ። ተፈሪ ፡ መኰንን ፡ ሐምሌ ፲፮ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ፡ ከአባታቸው ፡ ከልዑል ፡ ራስ መኰንን ፡ እና ፡ ከእናታቸው ፡ ከወይዘሮ ፡ የሺ ፡ እመቤት ፡ ጎሮ ፡ በተባለ ፡ የገጠር ፡ ቀበሌ ፡ ሐረርጌ ፡ ውስጥ ፡ ተወለዱ።
==
ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ | |
---|---|
ሃይለስላሴ በፊልድ ማርሻል ልብስ | |
ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ | |
ግዛት | ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ ፡ መስከረም ፪ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. |
በዓለ ንግሥ | ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. |
ቀዳሚ | ንግሥት ፡ ዘውዲቱ፣ |
ተከታይ | ዓፄ ፡ አምሃ ፡ ሥላሴ (በስደት) |
ባለቤት | እቴጌ ፡ መነን |
ልጆች | ልዕልት ፡ ሮማንወርቅ ልዕልት ፡ ተናኜወርቅ ዓፄ ፡ አምሀ ፡ ሥላሴ ልዕልት ፡ ዘነበወርቅ ልዕልት ፡ ፀሓይ ልዑል ፡ መኮንን ልዑል ፡ ሣህለ ፡ ሥላሴ |
ሙሉ ስም | ራስ ፡ ተፈሪ ፡ መኮንን |
ሥርወ-መንግሥት | ሰሎሞን |
አባት | ራስ ፡ መኮንን ፡ ወልደ ሚካኤል ፡ ወልደ መለኮት |
እናት | ወ/ሮ ፡ የሺመቤት ፡ አሊ |
የተወለዱት | ሐምሌ ፲፯ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም., መንግሥተ ኢትዮጵያ |
የሞቱት | ነሐሴ ፳፩ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም., መንግሥተ ኢትዮጵያ |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ክርስትና |
==
በ፲፰፻፺፱ ፡ የሲዳሞ ፡ አውራጃ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. ፡ የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሲሆኑ ፣ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሺህ ፡ ተከታዮች ፡ ነበሩዋቸውና ፡ ልጅ ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ በኅይል ፡ እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ አገረ ፡ ገዥነት ፡ እንዳይሽሯቸው ፡ የሚል ፡ ስምምነት ፡ ተዋዋሉ። ዳሩ ፡ ግን ፡ እያሱ ፡ ሃይማኖታቸውን ፡ ከክርስትና ፡ ወደ ፡ እስልምና ፡ እንደቀየሩ ፡ የሚል ፡ ማስረጃ ፡ ቀረበና ፡ ብዙ ፡ መኳንንትና ፡ ቀሳውስት ፡ ስለዚህ ፡ ኢያሱን ፡ አልወደዱዋቸውም ፡ ነበር። ከዚህም ፡ በላይ ፡ እያሱ ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ ከአገረ ፡ ገዥነታቸው ፡ ለመሻር ፡ በሞከሩበት ፡ ወቅት ፡ ስምምነታቸው ፡ እንግዲህ ፡ ተሠርዞ ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ ለወገናቸው ፡ ከስምምነቱ ፡ ተለቅቀው ፡ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ እሳቸው ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ አስወጡ። እንግዲህ ፡ በ፲፱፻፱ ፡ ዓ.ም. ፡ መኳንንቱ ፡ ዘውዲቱን ፡ ንግሥተ ፡ ነገሥት ፡ ሆነው ፡ አድርገዋቸው ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ እንደራሴ ፡ ሆኑ። ከዚህ ፡ ወቅት ፡ ጀምሮ ፡ ተፈሪ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ባለሙሉ ፡ ሥልጣን ፡ ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፩ ፡ ዓ.ም. ፡ የንጉሥነት ፡ ማዕረግ ፡ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ፡ ንግሥት ፡ ዘውዲቱ ፡ አርፈው ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ሆኑና ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ፡ ብዙ ፡ የውጭ ፡ ልዑካን ፡ በተገኙበት ፡ ታላቅ ፡ ሥነ-ሥርዓት ፡ ቅብዓ ፡ ቅዱስ ፡ ተቀብተው ፡ እሳቸውና ፡ ሚስታቸው ፡ እቴጌ ፡ መነን ፡ ዘውድ ፡ ጫኑ።
በንግሥ ፡ በዓሉ ፡ ዋዜማ ፡ ጥቅምት ፳፪ ፡ ቀን ፡ የትልቁ ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ የዳግማዊ ፡ ዓፄ ፡ ምኒልክ ፡ ሐውልት ፡ በመናገሻ ፡ ቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ ፡ ቤተ-ክርስቲያን ፡ አጠገብ ፤ ለዘውድ ፡ በዓል ፡ የመጡት ፡ እንግዶች ፡ በተገኙበት ፡ ሥርዐት ፣ የሐውልቱን ፡ መጋረጃ ፡ የመግለጥ ፡ ክብር ለብሪታንያ ፡ ንጉሥ ፡ ወኪል ፡ ለ(ዱክ ፡ ኦፍ ፡ ግሎስተር) ፡ ተሰጥቶ ፡ ሐውልቱ ፡ ተመረቀ።
ለንግሥ ፡ ስርዐቱ ፡ ጥሪ ፡ የተደረገላቸው ፡ የውጭ ፡ አገር ፡ ልኡካን ፡ ከየአገራቸው ፡ ጋዜጠኞች ፡ ጋር ፡ ከጥቅምት ፰ ፡ ቀን ፡ ጀምሮ ፡ በየተራ ፡ ወደ ፡ አዲስ ፡ አበባ ፡ ገብተው ፡ ስለነበር ፡ ሥርዓቱ ፡ በዓለም ፡ ዜና ፡ ማሰራጫ ፡ በየአገሩ ፡ ታይቶ ፡ ነበር። በተለይም ፡ በብሪታንያ ፡ ቅኝ ፡ ግዛት ፡ በጃማይካ ፡ አንዳንድ ፡ ድሀ ፡ ጥቁር ፡ ሕዝቦች ፡ ስለ ፡ ማዕረጋቸው ፡ ተረድተው ፡ የተመለሰ ፡ መሢህ ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ይሰብኩ ፡ ጀመር። እንደዚህ ፡ የሚሉት ፡ ሰዎች ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ስለ ፡ ፊተኛው ፡ ስማቸው ፡ «ራስ ፡ ተፈሪ» ፡ ትዝታ ፡ ራሳቸውን ፡ «ራስታፋራይ» ፡ (ራሰተፈሪያውያን) ፡ ብለዋል።
ዓጼ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዘውድ ፡ እንደጫኑ ፡ የአገሪቱን ፡ የመጀመሪያ ፡ ሕገ-መንግሥት ፡ እንዲዘጋጅ ፡ አዝዘው ፡በዘውዱ ፡ አንደኛ ፡ ዓመት ፡ በዓል ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፬ ፡ ዓ.ም. ፡ በአዲሱ ፡ ምክር ፡ ቤት ፡ (ፓርላማ) ፡ ለሕዝብ ፡ ቀረበ። ከዚህም ፡ በላይ ፡ ብዙ ፡ የቴክኖዎሎጂ ፡ ስራዎችና ፡ መሻሻያዎች ፡ ወደ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ከውጭ ፡ አገር ፡ አስገቡ።
በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. ፡ የሙሶሊኒ ፡ ፋሺስት ፡ ሠራዊት ፡ ኢትዮጵያን ፡ በወረረ ፡ ጊዜ ፡ ጃንሆይ ፡ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ፡ ከታገሉ ፡ በኋላ ፡ የጠላቱ ፡ ጦር ፡ ኅይል ፡ ግን ፡ በመጨረሻ ፡ ወደ ፡ እንግሊዝ ፡ አገር ፡ ለጊዜው ፡ አሰደዳቸው። ወደ ፡ ጄኔቭ ፡ ስዊስ ፡ ወደ ፡ ዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ማኅበር ፡ ሄደው ፡ ስለ ፡ ጣልያኖች ፡ የዓለምን ፡ እርዳታ ፡ በመጠየቅ ፡ ተናገሩ። የዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ግን ፡ ብዙ ፡ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ፡ ግን ፡ አውሮፓ ፡ ሁሉ ፡ በሁለተኛው ፡ የዓለም ፡ ጦርነት ፡ ተያዘ። የእንግሊዝ ፡ ሠራዊቶች ፡ ለኢትዮጵያ ፡ አርበኞች ፡ እርዳታ ፡ በመስጠት ፡ ጣልያኖች ፡ ተሸንፈው ፡ በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ፡ ኢትዮጵያን ፡ ተዉ። ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ አዲስ ፡ አበባን ፡ እንደገና ፡ የገቡበት ፡ ቀን ፡ ከወጡበት ፡ ቀን ፡ በልኩ ፡ ዕለት ፡ አምስት ፡ ዓመት ፡ በኋላ ፡ ነበረ።
ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ፡ የሕዝቦችን ፡ መብቶችና ፡ ተከፋይነት ፡ በመንግሥት ፡ አስፋፍቶ ፡ ሁለቱ ፡ ምክር ፡ ቤቶች ፡ እንደመረጡ ፡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፡ ግርማዊነታቸው ፡ የአፍሪካ ፡ አንድነት ፡ ድርጅት ፡ በአዲስ ፡ አበባ ፡ እንዲመሠረት ፡ ብዙ ፡ ድጋፍ ፡ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ፡ ወደ ፡ ካሪቢያን ፡ ጉብኝት ፡ አድርገው ፡ የጃማይካ ፡ ራስታዎች ፡ ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ በማርክሲስት ፡ አብዮት ፡ ደርግ ፡ ሥልጣን ፡ ያዙና ፡ እሳቸው ፡ በእሥር ፡ ቤት ፡ ታሰሩ። በሚከተለው ፡ ዓመት ፡ ከተፈጥሮ ፡ ጠንቅ ፡ እንደ ፡ አረፉ ፡ አሉ ፤ ሆኖም ፡ ለምን ፡ እንደ ፡ ሞቱ ፡ ስለሚለው ፡ ጥያቄ ፡ ትንሽ ፡ ክርክር ፡ አለ። ብዙ ፡ ራስታዎች ፡ ደግሞ ፡ አሁን ፡ እንደሚኖሩ ፡ ይላሉ።