የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት
From Wikipedia, the free encyclopedia
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አ.አ.ድ.) (እንግሊዝኛ፡ Organisation of African Unity (OAU))፣ (ፈረንሳይኛ፡ Organization de l'Unité Africaine (OUA))ግንቦት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ተመሥርቶ የድርጅቱ መመሪያ ውል (OAU Charter) በ፴፪ቱ መሥራች አገር መሪዎች ጸድቆ ተፈርሟል። የድርጅቱም ጠቅላይ መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ እንዲቆይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ግብዣ መሠረት እስካሁን ድረስ እዚያው አዲስ አበባ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በ፲፱፻፺፬ ዓ/ም ተደምስሶ የአፍሪካ ኅብረት በሚባለው ድርጅት ተተክቷል።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/0/07/Oau_banner.jpg/200px-Oau_banner.jpg)