Remove ads
From Wikipedia, the free encyclopedia
የኖህ ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 ይዘርዘራሉ።
በአዚህ መጽሐፍ ዘንድ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ከኖህ 3 ልጆች ከሴም ካምና ያፌትና ከሚስቶቻቸው ተወልደዋል ይባላል። ይህም በአውሮፓ ውስጥ በብዙዎቹ እስከ 19ኛ ክፍለ ዘመን ድረስ እንደ ታሪካዊ ዕውነት ይቆጠር ነበር። እስከ ዛሬም ድረስ በብዙ አይሁድ፣ እስላምና ክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዕውነተኛ ታሪክ ሆኖ ይታመናል።
የሴማውያን አባት ይባላል።
አፍሪካውያን እንግዲህ በጥንት የካም ልጆች ተባሉ። እስከ ዛሬ ኩሻውያን ወይም ኩሺቲክ ሕዝቦች ሲገኙ በምዕራብ አፍሪቃ የሚገኙት ዮሩባ ሕዝብ የትውልዳቸውን ሐረግ እስከ ካም ድረስ ያደርሱታል። ከ9ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ አንድ አይሁድ የስዋሰው መምህር ይሁዳ እብን ቁራይሽ እንደ አስረዳ የኩሺቲክና የሴሚቲክ ቋንቋ ቤተሠቦች ዝምድናን ያሳያሉ። ዛሬ የቋንቋ ጥናት ሊቃውንት እነዚህን ልሳናት ከግብጽኛ፣ በርበርኛ፣ ቻዲክ፣ እና ኦሞቲክ ቤተሠቦች ጋራ በአንድ ታላቅ አፍሮ-እስያዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ውስጥ ይጨምራሉ። በተጨማሪ በደቡባዊ አፍሪካ ያሉት ቤተሠቦች (እንደ ባንቱ) ከነዚህ የተለዩ ናቸው።
በአንዳንድ የድሮ እና ዘመናዊ አስተያየቶች ዘንድ የያፌት ስም ከሮማውያን አምላክ ዩፒተር ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚል ክርክር አቅርበዋል። ከዚህ በላይ ከግሪኩ አፈ ታሪካዊ ቅድማያት ከያፔቶስ ጋር ወይም ከሕንድ አፈ ታሪክ ሰው ከፕራ-ጃፓቲ ጋር ግንኙነት እንደ ነበራቸው የሚሉ ጽፈዋል።
በ1ኛ ክፍለ ዘመን የጻፈው ሮማዊ-አይሁድ ታሪከኛ ፍላዊዩስ ዮሴፉስ (ዮሴፍ ቤን-ማቲትያሁ) የአይሁዶች ጥንቶች በሚለው መጽሐፍ ውስጥ (1፣ 6) በዘፍጥረት 10 ላሉት ስሞች በየቀገኑ ለማስታወቅ ከሞከሩት አንድ ነው። እሱ የጻፋቸው መታወቂያዎች ለተከታተሉት ደራሲዎች መሠረት ሆነው እንዲህ ነበሩ[2]፦
የቅዱስ አቡሊዴስ ዜና መዋዕል (226 ዓ.ም.) በብዙ ሮማይስጥና ግሪክ ቅጂዎች ሲገኝ[3] በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 ላሉት ስሞች በየሕዝቡ መታወቂያ ለመስጠት እንደገና ይሞክራል። አንዳንዴ ከዮሴፉስ ውጤት ጋር ተመሳሳይ ቢሆን ልዩነቶቹ ግን ሰፊ ናቸው፣ እነሱም፦
የ346 ዓ.ም. ዜና መዋዕል፣ በክርስቲያን ጸሐፊ ኤጲፋንዮስ ዘሳላሚስ የተጻፈው መጽሐፍ ፓናርዮን (367 ዓ.ም. ገደማ)፣ የፋሲካ ዜና መዋዕል (619 ዓ.ም.)፣ የጅዮርጅያ ታሪከኛ ሙሴ ካጋንካትቫትሲ (7ኛው ክፍለ ዘመን) የጻፈው የአልባንያ ታሪክ እና ዮሐንስ ስኩሊትዜስ የጻፈው የታሪኮች መደምደምያ (1049 ዓ.ም.) ሁሉ የአቡሊዴስን መታወቂያዎች የከተላሉ።
በ382 ዓ.ም. ገዳማ የጻፉት ቅዱስ ሄሮኒሙስ (ጀሮም) በጻፉት ጽሕፈት ዕብራይስጥ ጥያቄዎች በዘፍጥረት የዮሴፉስን መታወቂያዎች በአዲስ ዝርዝር አወጣ። የሄሮኒሙስ ዝርዝር በተግባር እንደ ዮሴፉስ ዝርዝር ይመስላል፤ እነዚህ ልዩነቶች ግን አሉ፦
ጳጳሱና መምኅሩ ኢሲዶሬ ዘሰቪሌ 600 ዓ.ም. ገደማ በጻፉት ኤቲሚሎጊያይ የሄሮኒሙስን መታወቂያዎች ሁሉ ይደግማል፣ ከነዚህ ጥቃቅን ልዩነቶች በቀር፦[4]:
የኢሲዶሬ መታወቅያዎች ለያፌት ልጆች እንደገና በሂስቶሪያ ብሪቶኑም ይገኛሉ። የኢሲዶሬ መታወቂያዎች ደግሞ ለብዙ ኋለኞች መካከለኛ ዘመን መምህራን መሠረት ሆኑ።
በዘፍጥረት 10 የሚገኘው ትውልድ መጽሐፍ፣ የልጆቹ ስሞች 70 ወይም 72 አገሮችና ቋንቋዎች ሆኑ። ይህ እምነት ለረጅም ዘመን ሳይጠየቅ ተቀበለ። ነገር ግን በቅርቡ ክፍለ ዘመናት የቋንቋ ጥናት ሲመሠረት አዳዲስ ጥያቄዎች በአውሮፓ ተፈጠሩ። ጥያቄዎች የተነሡባቸው ዋን ምክንያቶች፦
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ኖኅ ከሴም ካምና ያፌት ጭምር ሌላ ልጅ እንደ ተወለደለት የሚናገሩ ልዩ ልዩ ታሪኮች ይገኛሉ። በነዚህ ምንጮች ዘንድ ተጨማሪው ልጅ የሚወለደው ወይም ከማየ አይህ በፊት፣ ወይም በኋላ (ወይም በውሃው ጊዜ እራሱ) በመሆን ይለያል።
በቁራን ሱራ «ሁድ» ዘንድ (11፡42-43) በመርከቡ እንዳይሣፈር እምቢ ያለ ሌላ ወንድ ልጅ ለ ኖኅ ነበረው። በመርከቡ በመሣፈር ፈንታ እሱ በተራራ ወጣና ሰመጠ። አንዳንድ የእስልምና ጸሐፊ ስሙ ወይም ያም ወይም ከነዓን እንደ ነበር ጽፏል።
በአይርላንድ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ በመርከቡ ለመሣፈር ያልተፈቀደ ቢጥ የተባለ ሌላ ወንድ ልጅ ለኖኅ ነበረው። በዚህ ታሪክ መሠረት ቢጥ ከዚያ በኋላ ወደ አይርላንድ ከነቤተሠቡ (በጠቅላላ 54 ሰዎች) ቢፈልሱም፣ ሁላቸው በማየ አይኅ ግን ሰጠሙ።
በ9ኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. በተጻፈ የአንግሎ-ሳክሰን ዜና መዋዕል ዘንድ፣ ሼይፍ የዌሰክሽ ሥርወ መንግሥት ቅድማያት ሲባል በመርከቡ ላይ የተወለደ የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ መሆኑ ይነገራል። በ1112 ዓ.ም. ገደማ ዊልያም ኦፍ ማልምዝቡሪ የእንግሊዝ ነገሥታት ትውልድ ጽፎ ግን ይህ ሼይፍ በመርከቡ ላይ ከተወለደው ከኖህ አራተኛው ወንድ ልጅ ከስትሬፊዩስ ዘር እንደ ነበር ብሏል።
ኪታብ አል-ማጋል የተባለው ጥንታዊ አረብኛ መጽሐፍ (ከ«ቄሌምንጦስ መጻሕፍት» መሃል) እንደሚለው የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ ቡኒተር ከማየ አይኅ ቀጥሎ ተወልዶ ሥነ ፈለክም ፈጥሮ የናምሩድ አስተማሪ ሆነ[5]። ለዚህ ተመሳሳይ ታሪኮች ለኖህ አራተኛ ልጅ የተለያዩ አጠራሮች ሲሰጡት ይታያል። ከነዚህም ጥንታዊው የግዕዝ ሰነድ መጽሐፈ አዳምና ሕይዋን (ስሙ ባርዊን ሆኖ)፤ ጥንታዊው የጽርዕ ሰነድ የመዝገቦች ዋሻ (ዮንቶን)፤ ፕሲውዶ- ('ሐሰተኛ') ሜቶድዮስ በተባለው ሰነድ (ዮኒቱስ[6])፣ በጽርዕ በ1213 ዓ.ም. የተጻፈው መጽሐፈ ንቡ (ዮናቶን)፤ በዕብራይስጥ በ12ኛው-14ኛው መቶ ዘመን አካባቢ የተጻፈው የይረሕምኤል ዜና መዋዕል (ዮኒጠስ)፣ እና በበርካታ አርሜንኛ ራዕዮች ውስጥ ማኒቶን ይባላል። ከዚህም በላይ ስለ ኖህ 4ኛ ወንድ ልጅ ተመሳሳይ ታሪኮች በጸሐፊዎቹ ጴጥሮስ ኮሜስቶር በ1152 ዓ.ም. ገደማ (ዮኒጡስ)፣ ጎድፍሬይ ዘቪቴርቦ 1177 ዓ.ም. (ኢሆኒቱስ)፤ ሚካኤል ሶርያዊው 1188 ዓ.ም. (ማኒቶን)፤ አቡ ሳሊኅ አርመናዊው 1200 ዓ.ም. ገደማ (አቡ ናይጡር)፤ ያዕቆብ ቫን ማይርላንት 1232 ገደማ (ዮኒቱስ)፤ አብርሃም ዛኩቶ 1496 ዓ.ም. (ዮኒኮ) እና ይሒኤል ቤን ሰሎሞን ሃይልፕሪን 1689 ዓ.ም. ገደማ (ዩኒኩ)።[7]
ማርቲን ዘኦፓቫ (1240 ዓ.ም. ገደማ)፣ የሚራቢሊያ ዑርቢስ ሮማይ ኋለኛ ቅጂዎች፣ እና የጆቫኒ ዲ ማሪንዮላ ክሮኒኮን ቦሄሞሩም (1347 ዓ.ም.) ሁላቸው ሲስማሙ፣ ወደ ጣልያን አገር ፈልሶ ሥነ ፈለክን ፈጥሮ ናምሩድንም ያስተማረው የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ ያኑስ ነበረ (የሮማ አረመኔው አምላክ 'ያኑስ' ሆነ ለማለት ነው)።
በመነኩሴው አኒዮ ዳ ቪቴርቦ ዘንድ (1490 ዓ.ም.)፣ በግሪኮች ዘመን (~300 ዓክልበ) በባቢሎን የጻፈው ታሪከኛ ቤሮሶስ ለኖኅ ከማየ አይኅ በኋላ 30 ልጆች እንደ ተወለዱለት ጽፎ ነበር። ከነዚህም መካከል ቱዊስኮን፣ ጵሮሜጤዎስ፣ ያፔቶስ፣ ማክሮስ፣ «16 ቲታኖች»፣ ክራኖስ፣ ግራናዎስ፣ ውቅያኖስ እና ቲፌዮስ የተባሉ ወንድ ልጆች በስም ይጠቀሳሉ። ደግሞ የኖኅ ሴት ልጆች አራክሳ «ታላቂቱ»፣ ሬጊና፣ ፓንዶራ፣ ክራና እና ጤቲስ ይባላሉ። ነገር ግን አኒዮ ያገኘው ሰነድ የቤሮሶስ ሳይሆን ሐሰተኛ መሆኑ ዛሬ አይጠረጠርም[8]።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.