ኢየሱስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישוע ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት (በግሪክ ቋንቋ ሲጻፍ Χριστός ፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው)፤ (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም ዐማኑኤል ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው ። ከሥላሴ አንዱ አካል ወልድ ኢየሱስ ነው።
Quick Facts የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ, ነዋ በግዑ ለእግዚብሔር ዘይሐትት ወያሰስል ኃጢያተ ዓለም ...
የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ | |
---|---|
ነዋ በግዑ ለእግዚብሔር ዘይሐትት ወያሰስል ኃጢያተ ዓለም | |
የተወለደው |
በ፩ኛው ዓ.ም. በቤተልሔም ዓመተ ምሕረትም ስለሱ ተቆጠረ |
የእናት ስም |
ማርያም |
የአባት ስም |
እግዚአብሔር አብ (ያሳደገው ቅዱስ ዮሴፍ እንደ አባት) በሰማይ መንፈሳዊ እናት በምድር ሥጋዊ አባት የለውም |
ዓመታዊ ዋና በዐላት |
፱ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ ገና (ልደት) ጥምቀት ስቅለት ትንሳዔ (ፋሲካ) |
ያደገበት ቦታ | ናዝሬት-ገሊላ |
ያረፈው | በ፴፫ኛው ዓ.ም. በእየሩሳሌም |
ከሙታን ተለይቶ የተነሳው | ባረፈ በ፫ኛው ቀን በእየሩሳሌም |
የሚመለከው | በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ ሕዝብ [1] |
Close
ኢየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለትም ከሥላሴ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ
እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ።
ከድረ ገጾቹ አንዱን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ
እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።