![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/3/31/%25E1%2589%2585%25E1%258B%25B1%25E1%2588%25B5_%25E1%2588%259B%25E1%2588%25AD%25E1%2589%2586%25E1%2588%25B5%25E1%258D%25B4.jpeg/640px-%25E1%2589%2585%25E1%258B%25B1%25E1%2588%25B5_%25E1%2588%259B%25E1%2588%25AD%25E1%2589%2586%25E1%2588%25B5%25E1%258D%25B4.jpeg&w=640&q=50)
የማርቆስ ወንጌል
From Wikipedia, the free encyclopedia
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ማርቆስ እንደ ጻፈው። ቅዱስ ማርቆስ ወንግልን ለመስበክ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ወደ ሮም ተጉዞ ቀዳሚ የወንጌል ፀሐፊ ሆነ ። (፩ኛ ጴጥ ም፡፭ ቁ፡፲፪- ፲፫) ከጌታ የሰማውንና የተማረውን ጽፎአል። ወንጌልንም የጻፈበት ዘመን ጌታ ከዐረገ አሥራ አንደኛው ተፈፅሞ አሥራ ሁለተኛው ሲጀምር፣ ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በአራተኛው ዓመት ሲሆን ወንጌል ተብሎ ይፋ የወጣበት ቋንቋ ሮማይስጥ ነው ማለት ቅዱስ ጴጥሮስ በሮማይስጥ አስተርጉሞ የሮማ ሰዎችን ለማስተማር ተጠቅሞበታል ። ወንጌሉም ቅዱስ ማርቆስ ካለፈ በኋላ በስሙ ተጠርቷል።
Quick Facts ቅ.ማርቆስ ወንጌላዊው, የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ...
ቅ.ማርቆስ ወንጌላዊው | |
---|---|
![]() | |
የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል | |
የፀሐፊው ስም | ዮሐንስ በኋላ ማርቆስ |
የተወለደበት ቀን | ጥቅምት ፴ በ፩ኛው ክፍለዘመን |
የተወለደበት ቦታ | ሲሬን (ሰሜን አፍሪካ) |
የእናት ስም | ማርያም ብሉይ ኪዳንን ማለት የሃይማኖት ትምህርት በዕውቅ ት/ቤት እንዲማር ምክኒያት የሆነች ትልቅ ሴት ናት ዕብራዪስጥና ዮናይስጥ ይጽፋል ይናገራል |
የአባት ስም | አሪስቶፑለስ |
በዓለንግሥ | ሚያዝያ ፴ |
ምልክት |
![]() |
ሥራው | ፀሐፊ ሰባኪም |
የሚከበረው | በዓለም ክርስቲያን ሕዝብ [1] |
የጻፈው ወንጌል | ፲፮ ምዕራፍ |
ያረፈበት ቀን | ሚያዝያ ፴[2] |
← የማትዮ.ወንጌ የሉቃስ.ወንጌ → | |
Close
ቀጥሎም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በግብፅ አገር ተልኮውን ማኪያሄድ እንዳለበት ተረድቶ እዚሁ አገር ላይ የአንበሳ ጣዖቶችን በማጥፋት የነገደ ይሁዳ የሆነውን አንበሳ ክርስቶስን በመስበክ ከዚያም የመጀመሪያው ጳጳስ ሆኖ በመናፍቃን ተገድሎ በሰማዕትነት ያለፈ ቅዱስ ነው። ይህ ክርስቲያናዊ ተጋድሎ ነው የአንበሳ ምልክት እንዲሰጠው ዋና ምክኒያት የሆነው። በተጨማሪ በራዕዪ ዮሐንስ (፭፡፭) ጌታች መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አሸናፊ የይሁዳ አንበሳ ተብሎ ተሰይሟል ፣ በነብዩ በሆሴዕ (፲፫፡፯) አንበሳ ተብሎ መጠራቱን እናያለን [3] ።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/2/25/%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5_%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%89%86%E1%88%B5.png/320px-%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5_%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%89%86%E1%88%B5.png)