የዥዎሉ ውግያቻይና ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ በ2331 ዓክልበ. ግድም በዥዎሉ አካባቢ የተደረገ ታልቅ ውግያ ነበረ። ይህ ከባንጯን ውጊያ (2350 ዓክልበ. ግድም) በኋላ ትቂት ዓመታት በኋላ ይሆናል።

ብሔሮች በዥዎሉ ውግያ ዘመን ያህል

በዚሁ ውግያ የኋንግ ዲ ኃያላት (የኋሥያ ወገን) በቺ ዮው ሠራዊት ላይ ድል አደረጉ። ይህ ቺ ዮው የ81 ጎሣዎች አለቃ ነበር ይባላል። በውግያው ቺ ዮው ጉምን በጥንቆላ ፈጥሮ ኋንግ ዲ «ደቡብ አመልካች ሠረገላ» የተባለውን ጠድከል ፈጠረ፣ በእርሱም እርዳታ ደብዛቸውን አገኙ። ብዙም ሌሎች ጉድ ሥራዎች እንደ ተከሠቱ የሚል ወሬ አለ። በመጨረሻ ቺ ዮው ተገድሎ ወገኑ እንደ ተከፋፈለ ይታመናል። አንዱ ወገን በያንግ-ጸ ወንዝ ደቡብ ቀርቶ የህሞንግ (ምያው) ብሔር ወላጆች ሆኑ።

ነገር ግን የኮርያን ልማዳዊ አፈታሪክ የሚገልጸው መጽሐፍ ኋንዳን ጎጊ ከዚህ ሌላ ታሪክ አለው። ቺ ዮው «ጃውጂ ኋኑንግ» ተብሎ «ሺንሺ» ወይም «ፔዳል» የተባለ መንግሥት በአሁኑ ስሜን ኮርያ መሠረተ፣ የኋንግ ዲም ግዛት ከዥዎሉ ምዕራብ ነበር። በዥዎሉ (ኮሪይኛ ታክሮክ) ውግያ ድል ያደረገው ወገን የቺ ዮው ሠራዊት ነበር፣ ኋንግ ዲንም ማረኩት ለቺ ዮውም ተገዥ አደረጉት። የሺንሺ ሰዎች የኮርያ ብሔር ወላጆች እንደ ሆኑ ይላል።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.