From Wikipedia, the free encyclopedia
ኋንግ ዲ (ቻይንኛ፦ 黃帝 «ቢጫው ንጉሥ») በቻይና ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ የቻይና ሕዝብ አባትና ንጉሥ ነበረ። የቤተሠቡ ስም «ጎንግሱን» የተሰጠው ስም «ሽወንዩወን» ነበር ይባላል። አባቱ ሻውድየን ተባለ።
የተወለደው ሾው ጪው በተባለ ሥፍራ በጩፉ ሲሆን በኋላ ነገዱን ወደ ዥዎሉ ወሰደው፤ በዚያ ገበሬ ሆኖ ድብ፣ ነብርና ባለክንፍ አንበሣ የመሰለ ፍጡር አንዳስለመደ የሚል ትውፊት አለ። ያንጊዜ የኋንግ ዲ ወገን እና የያንዲ (ዩዋንግ) ወገን ለቢጫው ወንዝ ሸለቆ ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ሦስተኛ ወገን - የሊ ሕዝብና ንጉሣቸው ቺ ዮው - ደግሞ ጠላቶቻቸው ሆኑ። ሦስት ውግያዎች ተከተሉ። በመጀመርያው የቺ ዮው ሥራዊት ያንዲውን አሸነፈው። ከዚያ ያንዲው ተሸንፎ ወደ ኋንግ ዲ ሸሸ። በሁለተኛው የዥዎሉ ውግያ ኋንግ ዲ እና ቺ ዮው ተጋጠሙ። በዚህ ውግያ ቺ ዮው ጉምን በጥንቆላ ፈጥሮ ኋንግ ዲ እንደገና በተነው፣ ብዙም ሌሎች ጉድ ሥራዎች እንደ ተከሠቱ የሚል ትውፊት አለ። ቺ ዮው በዚህ ውግያ ቢሸነፍም፣ የኮርያ ሕዝብና የህሞንግ ሕዝብ ዛሬውንም እንደ ቅድማያታቸው ይቆጥሩታል። በሦስተኛው የባንጯን ውግያ፣ ኋንግ ዲ በያንዲው ላይ ድል አደረገ። ከዚያ በኋላ ወገኖቻቸው ተባብረው የኋሥያ ብሔር (የቻይና ሕዝብ ቅድማያቶች) ፈጠሩ። ኋንግ ዲ በይፋ የቻይና ንጉሥነት ማዕረግ ወሰደ፤ የዘውድና ቤተ መንግሥት ሥርዓት ጀመረ።
ከዚህ በተረፈ ኋንግ ዲ ጋሪና መርከብ እንደ ፈጠረ ይጻፋል። ደግሞ ምኒስትሩ ጻንግችየ መጀመርያ የቻይና ጽሕፈት ፈጠረ፤ የኋንግ ዲ ሚስት ሌዙም ልብስ ከሃር ትል እንዴት እንደሚሠራ አሳየች። የህክምና መጽሓፍ ኋንግዲ ኔጂንግ ሌሎችንም መጻሕፍት እንደ ጻፈ ይታመናል። ከዚህ በላይ የቻይና ስነ ፈለክና የቻይና ዘመን አቆጣጠር ፈጠረ። ስለ ኋንግ ዲ ብዙ ሌሎች ትውፊቶች አሉ።
መጀመርያ ሚስቱ ሌዙ ተከታዩን ሻውሃውን ወለደች። 3 ሌሎች ሚስቶች እነርሱም ፋንግሌ፣ ቶንግዩ እና ሞሙ ነበሩት። በተለመደው ታሪክ ዘንድ ለ99 አመት ነገሠ። ታላቅ መቃብሩ በያንአን ከተማ ሲገኝ እስከ ዛሬ ድረስ በየአመቱ በሥነ ስርአት ይከብራል።
የቀርከሃ ዜና መዋዕል የሚባሉት ጥንታዊ መዝገቦች በኋንግ ዲ ዘመን ይጀምራሉ።
ኋንግ ዲ 7 አመት ከአረፈ በኋላ፣ ሚኒስትሩ ጻንግችየ ዧንሡን ንጉሥ እንዳደረገው ይባላል።
ቀዳሚው የለም (መሥራች) |
የኋሥያ (ቻይና) ንጉሥ | ተከታይ ሻውሃው |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.