![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/b/bb/Wolayita.jpg/640px-Wolayita.jpg&w=640&q=50)
ዎላይታ
የኢትዮጵያ ዞን አስተዳደር / From Wikipedia, the free encyclopedia
ዎላይታ ወይም ወላይታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የአስተዳደር ዞን ነው። የዞኑ ስያሜ በዞኑ ውስጥ ካለው የወላይታ ህዝብ ተሰይሟል። ወላይታ በደቡብ ጋሞ ዞን ፣ በምዕራብ ከዳውሮ ዞን ሲሆን የሚለየው የኦሞ ወንዝ ፣ በሰሜን ምዕራብ በከምባታ ፣ በሰሜን በሐዲያ ፣ በሰሜን ምስራቅ በኦሮሚያ ክልል ፣ በምስራቅ ሲዳማ ክልል ፣ በደቡብ ምስራቅ በኩል ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል ይዋሰናል። በደቡብምስራቅ በኩል ኦሮሚያና ዎላይታ የሚለየው የአባያ ሀይቅ ነው። የዎላይታ አስተዳደር ማዕከል ሶዶ ነው። ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች አረካ ፣ ቦዲቲ ፣ ጠበላ ፣ ባሌ ሀዋሳ ፣ ገሱባ ፣ ጉኑኖ ፣ በዴሳ እና ዲምቱ ናቸው።
Quick Facts
ዎላይታ ዞን Wolaytta Moottaa | |
![]() | |
![]() | |
ሀገር | ![]() |
ክልል | ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት |
ዋና ከተማ | ሶዶ |
ዋና አስተዳዳሪ | ሳሙኤል ፎላ |
የቦታ ስፋት | |
• አጠቃላይ | 451,170.7 |
ድረ ገጽ | www |
Close
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/8/80/Map_of_zones_of_Ethiopia.svg/640px-Map_of_zones_of_Ethiopia.svg.png)
ዎላይታ 358 ኪሎ ሜትር (222 ማይል) በሁሉም ወቅቶች የሚመች መንገድ እና 425 ኪሎ ሜትር (264 ማይል) ደረቅ መንገዶች፣ በአማካይ የመንገድ ጥግግት 187 ኪሎ ሜትር በ1000 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው። [1] በዎላይታ ውስጥ ከፍታ ቦት ዳሞታ ተራራ ሲሆን ከፍታው 2738 ሜትር ነው።