ሳት
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ ሷ
ሳት (ወይም ሰዓት) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 15ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ ፊደሎች 15ኛው ፊደል "ሳሜክ" በሶርያም ፊደል "ሲምኬት" ይባላል። በዓረብኛ ግን ተመሳሳይ ፊደል የለም፣ ለዚሁ ድምፅ ከ"ሺን" የተወሰደ ፊደል በሱ ፈንታ አለ።
በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ "ሳት" ከ"ሠውት" (ሠ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን በግዕዝ የ"ሠውት" ድምጽ "ሸ" ለማመልከት ይጠቅም ነበር። በዛሬው አማርኛ "ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ" ከ"ሰ..." ትንሽ ተቀይሯል።