ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ



More information የአቡጊዳ ታሪክ ...
Close

ዋዌ (ወይም ዋውወዌ) በአቡጊዳ ተራ ስድስተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች ስድስተኛው ፊደል «ዋው» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ «ዋው» በ«አብጃድ» ተራ 6ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 27ኛው ነው።)

በዘመናዊ ዕብራይስጥ «ዋው» (ו) ተናባቢ ሲሆን እንደ «ቭ» ይሰማል። አናባቢ ሲሆን ግን «ኡ» ወይም «ኦ» ያመለክታል።

ታሪክ

More information ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል, ቅድመ-ሴማዊ ...
ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
T3
Close


የዋዌ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ «ሐጅ» ነበር።

More information ከነዓን, አራማያ ...
ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ዋው ዋው ו ዋው و
Close


የከነዓን «ዋው» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም «ዋው» ወለደ።

ከዚህ በላይ የከነዓን «ዋው» የግሪክ አልፋቤት «ዲጋማ» («ዋው») (Ϝ ϝ) አባት ሆነ፤ የ«ው» ድምጽ ግን ቀድሞ ከቋንቋው ጠፍቶ ዲጋማ እንደ ቁጥር ብቻ ጠቀመ። (ደግሞ ስቲግማ ይዩ።) በላቲን አልፋቤት ግን (F f) ከዲጋማ ተነሣ።

በኋላ ዘመን የከነዓን «ዋው» እንደገና የግሪክ «ኡፕሲሎን» (Υ υ) ወለደ። ይህም የላቲን አልፋቤት (V v) እና (Y y) እና የቂርሎስ አልፋቤት (У, у) ወላጅ ሆነ። እንደገና የላቲን ፊደሎች (U u) እና (W w) ከ«V» ስለተነሡ እነዚህ ሁሉ የ«ዋዌ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.