From Wikipedia, the free encyclopedia
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ ቷ
ታው (ወይም ታዊ) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 22ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 22ኛው ፊደል "ታው" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ታእ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 22ኛ ነው።
በአማርኛ ደግሞ "ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ" ከ"ተ..." ትንሽ ተቀይሯል።
የታው መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመስቀል ስዕል መስለ። ይህን የመሰለው ሃይሮግሊፍ በጥንታዊ ግብጽኛ "ሰውእ" ነበር።
የከነዓን "ታው" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ ታው የአረብኛም "ታእ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ታው" (Τ, τ) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (T t) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Т т) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ"ታው" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.