አዕላፍ
From Wikipedia, the free encyclopedia
አዕላፍ (ምልክቱ: ∞) በብዙ የትምህርት መስኮች ዘንድ ወሰን የለሽ፣ ወይንም ማብቂያ የለሽ መስፈርትን ለመወከል የሚረዳ ጽንሰ ሐሳብ ነው።
በሒሳብ ጥናት ውስጥ፣ አዕላፍ እንደቁጥር ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል (ማለቱ፦ ነገሮችን ለመለኪያ እና ለመቁጠሪያ ሲያገለግል ይታያል.. ለምሳሌ "አእላፍ ቁጥሮች")። ነገር ግን አዕላፍ እንደሌሎች ቁጥር አይደለም። የኢምንትን ጽንሰ ሐሳብ በሚጠቀልሉ የቁጥር ስርዓቶች ውስጥ አዕላፍ ማለቱ የኢምንት ግልባጭ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር 1 ሲካፍል ለኤምንት፣ አዕላፍን ይሰጣል። አዕላፍ ማለት እንግዲህ ከማናቸውም ነባር ቁጥር (ሪል ነምበር) የሚበልጥ ነው። አሁን ያለውን የአዕላፍ ጽንሰ ሐሳብ ስርዓት ያስያዘው ጆርጅ ካንተር ሲሆን ይሄውም በ 20ኛው ክፍለ ዘመን ዋዜማ ነበር። በዚህ አዲሱ ስርዓት የተለያዩ አዕላፍ ስብስቦች የብዛት ቁጥራቸው የተለያየ ሊሆን እንዲችል አሳይቷል[1] ለምሳሌ የድፍን ቁጥር (ኢንቲጀር) ስብስብ ተቆጣሪ አዕላፍ ሲሆን፣ የነባር ቁጥር ስብስብ ግን የማይቆጠር አዕላፍ እንደሆነ አሳይቷል።