ስር ፒተር አለክሳንደር ኡስቲኖቭ (ከሚያዚያ 1921 - መጋቢት 28 ቀን፣ 2004 እ.ኤ.አ.) የነበረ የእንግሊዝ ተዋናይ፣ ጸሃፊና ተውኔት ደራሲ ነበር። በተለይ ደግሞ ፊልም ሰሪቲያትር አዘጋጅ እና ኦፔራ መሪ፣ ፊልም አዘጋጅመድረክ ተላሚፊልም ደራሲቀልደኛኮሜዲያንጋዜጣ አዘጋጅመጽሔት አዘጋጅራዲዮ አስተላላፊቴሌቪዥን አቅራቢ ነበር።

Thumb
ፒተር ኡስቲኖቭ

ሰር ፒተር ኡስቲኖቭ በእናቱ በኩል የራሽያ ነገስታት ዘር ሲሆን በአባቱ በኩል ደግሞ የራሺያጀርመንኢትዮጵያ ነገስታት ዘር ነው። በራሱ በኡስቲኖቭ አስተያየት ቅደመ አያቱ የአጼ ቴወድሮስ ልጅናት[1] የሚል ሲሆን በአንዳንድ ተመራማሪወች ዘንድ ግን ቅድመ አያቱ ማግዳሊና ሀል የተባለች የወለተ እየሱስ (ካታሪና ሀል) ልጅ ናት። ወለተ እየሱስ የእቴጌ ጣይቱ አማካሪ የነበረች የቴወድሮስ መድፍ ሰሪ የነበረው ሞሪዝ ሆል የተሰኘ አይሁድ ሚስት ነበረች። ወለተ እየሱስ የጀርመኑ ሰዓሊ ኤድዋርድ ዛንደር እና እሳተ ወርቅ የተሰኘች የጎንደር ወታደር የነበርው መቃዶ ልጅ ናት። [2]

እጅግ ቅኔያዊ በሆኑ ንግግሮቹና ቀልዶቹ የታወቀው ይህ ሰው በቴሌቪዥን፣ በሌክቸርና በመሳሰሉት የህዝብ ስራወች ምንጊዜም አይጠፋም ነበር። በኋላም በነበረው የአይምሮ ብሩህነትና የዲፕሎማት ስራ አስተማሪ ሆኖ አገልግሏል፣ የዩኒሲኤፍም አምባሳደርና የአለም አቀፍ ፌዴራሊስት እንቅስቃሴም ፕሬዜዳንት ነበር።

ፒተር ኡስቲኖቭ የአካዳሚ አዋርድስ፣ ኤሚ አዋርድስ፣ ጎልደን ግሎብስና ባፍታ አዋርድስን አሸናፊ ሲሆን የመንግስት ሽልማትንም ከእንግሊዝፈረንሳይጀርመን አገሮች አግኝቷል። በ2004 ዓ.ም. ከሞተም በኋላ፣ የዱርሃም ዩኒቨርስቲ የድህረ ምረቃ ማህበረሰብን የኡስቲኖብ ኮሌጅ በማለት ሰይሟል።

ዋቢ ጽሕፈት

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.