From Wikipedia, the free encyclopedia
ፎገራ በደቡብ ጎንደር የሚገኝ ወረዳ ሲሆን፣ የወረዳው አስተዳደር ማዕከል ወረታ ይሰኛል። በዚህ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ታዋቂ ትናንሽ ከተሞች ውስጥ አመድ በር እና አውራአምባ ይገኛሉ።
ጉማራ እና ርብ ወንዝ ይህን ክፍል ሲያካልሉት ለጣና ሐይቅ ያለው ቅርበት ደግሞ የውሃ ሃብቱን ያጎላዋል። 490 ስኩየር ኪ.ሜ. እሚያክለው የዚህ ወረዳ መሬት በየአመቱ በጣና ሐይቅ ሙላት ምክንያት የጎርፍ ተጠቂ ነው። [2] ጤፍ፣ ማሽላ፣ ዳጉሳ፣ ጥጥ፣ ሰሊጥ ዋናዎቹ የዚህ ወረዳ ምርቶች ናቸው። የፎገራ ላም ለየት ያለ የላም ዝርያ ዓይነት ሲሆን በግዙፍነቱና በከፍተኛ የወተት ምርቱ ይታወቃል። ሆኖም በበጋ ወራት ከከምከም እና ደራ ወረዳዎች ላሞች ወደዚህ ወረዳ ለግጦሽ ስለሚመጡ የዚህ ዝርያ ላም በመዳቀል ኅልውናው አስጊ ሆኗል።
ፎገራ የአለቃ ገብረሃና የትውልድ ቦታ በመሆኑም ይታዎቃል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.