From Wikipedia, the free encyclopedia
የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፱ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የነበረ ሲሆን ከሰኔ ፬ እስከ ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ተካሄዷል። ውድድሩን ለማቅረብ የተካሄደው ዕጣ ውስጥ የአፍሪካ ሀገሮች ብቻ እንዲሳተፉ ነበር የተፈቀደው። ደቡብ አፍሪካ ግብፅና ሞሮኮን በማሸነፍ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫን ያቀረበች አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች።
የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ |
|
---|---|
ይፋዊ ምልክት
|
|
የውድድሩ ዝርዝር | |
አስተናጋጅ | ደቡብ አፍሪካ |
ቀናት | ከሰኔ ፬ እስከ ሐምሌ ፬ ቀን |
ቡድኖች | ፴፪ (ከ፮ ኮንፌዴሬሽኖች) |
ቦታ(ዎች) | ፲ ስታዲየሞች (በ፱ ከተማዎች) |
ውጤት | |
አሸናፊ | እስፓንያ |
ሁለተኛ | ኔዘርላንድስ |
ሦስተኛ | ጀርመን |
አራተኛ | ኡራጓይ |
እስታቲስቲክስ | |
የጨዋታዎች ብዛት | ፷፬ |
የጎሎች ብዛት | ፻፵፭ |
የተመልካች ቁጥር | 3,178,856 |
ኮከብ ግብ አግቢ(ዎች) | ዲዬጎ ፎርላን ቶማስ ሙለር ዌዝሊ ሽናይደር ዳቪድ ቪያ ፭ ጎሎች |
ኮከብ ተጫዋች | ዲዬጎ ፎርላን |
← 2006 እ.ኤ.አ. 2014 እ.ኤ.አ. → |
የማጣሪያ ዕጣ በኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻ ዓ.ም. በደርባን ከተማ ተካሄዷል። ደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅ ስለሆነች ያለ ማጣሪያ አልፋለች። ነገር ግን የ2006 እ.ኤ.አ. አሸናፊ ጣሊያን በማጣሪያው መሳተፍ ነበረባት።
ኤ.ኤፍ.ሲ. ካፍ |
ኮንካካፍ ኮንሜቦል ኦ.ኤፍ.ሲ. |
ዩኤፋ |
ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $420 ሚሊዮን ነው።[1] ይህም ከ2006 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የስልሳ ከመቶ ዕድገት አለው።[1] ከዚህ ውስጥ $40 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1 ሚሊዮን የተረከበ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ እንደሚመለከተው ተከፋፍሏል፦[1]
ግጥሚያዎቹ በዘጠኝ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አስር ስታዲየሞች ውስጥ ነው የተካሄዱት። የዋንጫ ጨዋታው በጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኘው ሶከር ሲቲ ስታዲየም ነው የተከናወነው።
ጆሃንስበርግ | ደርባን | ኬፕ ታውን | ጆሃንስበርግ |
---|---|---|---|
ሶከር ሲቲ | ሞዝስ ማቢዳ ስታዲየም | ኬፕ ታውን ስታዲየም | ኤሊስ ፓርክ ስታዲየም |
አቅም፦ 89,700 | አቅም፦ 70,000 | አቅም፦ 69,070 | አቅም፦ 62,567 |
ፕሪቶሪያ | ኔልስፕሩዊት | ||
ሎፍተስ ቨርስፌልድ ስታዲየም | ምቦምቤላ ስታዲየም | ||
አቅም፦ 51,760 | አቅም፦ 40,113 | ||
ፖርት ኤልሳቤጥ | ብሉምፎንቴይን | ፖሎክዋኔ | ሩስተንበርግ |
ኔልሰን ማንዴላ ቤይ ስታዲየም | ፍሪ ስቴት ስታዲየም | ፒተር ሞካባ ስታዲየም | ሮያል ባፎኬንግ ስታዲየም |
አቅም፦ 48,000 | አቅም፦ 48,070 | አቅም፦ 46,000 | አቅም፦ 44,530 |
የፊፋ አዘጋጅ ኮሚቴ የዕጣ አወጣጥ ሂደቱን በኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. አጸደቀ። የዘር ቡድኖች (seed teams) አደረጃጀት አዘጋጅ አገር ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በኦክቶበር 2009 እ.ኤ.አ. በወጣው የፊፋ የአገራት የብቃት ደረጃ ላይ የተመሰረተ ነው። በደረጃ ላይ ከ፩ እስከ ፯ የተቀመጡት ቡድኖች ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በቋት ፩ ተመድበዋል።
የመደብ ድልድል ሥነ ስርዓቱ በኬፕ ታውን፣ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ኬፕ ታውን ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል በኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ተከናወነ። ሥነ ስርዓቱ የቀረበው በደቡብ አፍሪካዊቷ ተዋናይ ሻርሊዝ ቴሮን እና የፊፋ ዋና ጸሐፊ ዠሮም ቫልክ ነው።[2] የዕጣ ኳሶቹን ያወጡት ዴቪድ ቤክሃም፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ጆን ስሚት፣ መካያ ንቲኒ፣ ማቲው ቡዝ እና ሲምፊዌ ድሉድሉ ናቸው።[3]
የፊፋ ዳኛዎች ኮሚቴ ፳፱ ዳኛዎችን ለዓለም ዋንጫ መርጧል። እነዚህም ከኤ.ኤፍ.ሲ. አራት፣ ከካፍ አስር፣ ከኮንሜቦል ስድስት፣ ከኮንካካፍ አራት፣ ከኦ.ኤፍ.ሲ. ሁለት እና ከዩኤፋ አስር ዳኛዎችን ያጠቃልላል።[4] እንግሊዛዊው ዳኛ ሀዋርድ ዌብ የዋንጫ ጨዋታውን እንዲዳኝ ተመርጧል።[5]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤ
ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ደቡብ አፍሪካ | 1 – 1 | ሜክሲኮ |
ኡራጓይ | 0 – 0 | ፈረንሣይ |
ሰኔ ፱ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ደቡብ አፍሪካ | 0 – 3 | ኡራጓይ |
ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ፈረንሣይ | 0 – 2 | ሜክሲኮ |
ሰኔ ፲፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ሜክሲኮ | 0 – 1 | ኡራጓይ |
ፈረንሣይ | 1 – 2 | ደቡብ አፍሪካ |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ
ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ደቡብ ኮሪያ | 2 – 0 | ግሪክ (አገር) |
አርጀንቲና | 1 – 0 | ናይጄሪያ |
ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
አርጀንቲና | 4 – 1 | ደቡብ ኮሪያ |
ግሪክ (አገር) | 2 – 1 | ናይጄሪያ |
ሰኔ ፲፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ናይጄሪያ | 2 – 2 | ደቡብ ኮሪያ |
ግሪክ (አገር) | 0 – 2 | አርጀንቲና |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ሲ
ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
እንግሊዝ | 1 – 1 | አሜሪካ |
ሰኔ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
አልጄሪያ | 0 – 1 | ስሎቬኒያ |
ሰኔ ፲፩ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ስሎቬኒያ | 2 – 2 | አሜሪካ |
እንግሊዝ | 0 – 0 | አልጄሪያ |
ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ስሎቬኒያ | 0 – 1 | እንግሊዝ |
አሜሪካ | 1 – 0 | አልጄሪያ |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ
ሰኔ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ሰርቢያ | 0 – 1 | ጋና |
ጀርመን | 4 – 0 | አውስትራልያ |
ሰኔ ፲፩ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ጀርመን | 0 – 1 | ሰርቢያ |
ሰኔ ፲፪ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ጋና | 1 – 1 | አውስትራልያ |
ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ጋና | 0 – 1 | ጀርመን |
አውስትራልያ | 2 – 1 | ሰርቢያ |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኢ
ሰኔ ፯ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ኔዘርላንድስ | 2 – 0 | ዴንማርክ |
ጃፓን | 1 – 0 | ካሜሩን |
ሰኔ ፲፪ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ኔዘርላንድስ | 1 – 0 | ጃፓን |
ካሜሩን | 1 – 2 | ዴንማርክ |
ሰኔ ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ዴንማርክ | 1 – 3 | ጃፓን |
ካሜሩን | 1 – 2 | ኔዘርላንድስ |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤፍ
ሰኔ ፯ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ኢጣልያ | 1 – 1 | ፓራጓይ |
ሰኔ ፰ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ኒው ዚላንድ | 1 – 1 | ስሎቫኪያ |
ሰኔ ፲፫ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ስሎቫኪያ | 0 – 2 | ፓራጓይ |
ኢጣልያ | 1 – 1 | ኒው ዚላንድ |
ሰኔ ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ስሎቫኪያ | 3 – 2 | ኢጣልያ |
ፓራጓይ | 0 – 0 | ኒው ዚላንድ |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ጂ
ሰኔ ፰ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ኮት ዲቯር | 0 – 0 | ፖርቱጋል |
ብራዚል | 2 – 1 | ሰሜን ኮርያ |
ሰኔ ፲፫ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ብራዚል | 3 – 1 | ኮት ዲቯር |
ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ፖርቱጋል | 7 – 0 | ሰሜን ኮርያ |
ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ፖርቱጋል | 0 – 0 | ብራዚል |
ሰሜን ኮርያ | 0 – 3 | ኮት ዲቯር |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤች
ሰኔ ፱ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ሆንዱራስ | 0 – 1 | ቺሌ |
እስፓንያ | 0 – 1 | ስዊዘርላንድ |
ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ቺሌ | 1 – 0 | ስዊዘርላንድ |
እስፓንያ | 2 – 0 | ሆንዱራስ |
ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. | ||
ቺሌ | 1 – 2 | እስፓንያ |
ስዊዘርላንድ | 0 – 0 | ሆንዱራስ |
ዋና መጣጥፍ፦ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ
የ፲፮ ዙር | ሩብ-ፍፃሜ | ግማሽ-ፍፃሜ | ፍፃሜ | |||||||||||
ሰኔ ፲፱ – ፖርት ኤልሳቤጥ | ||||||||||||||
ኡራጓይ | 2 | |||||||||||||
ሰኔ ፳፭ – ጆሃንስበርግ | ||||||||||||||
ደቡብ ኮርያ | 1 | |||||||||||||
ኡራጓይ (ቅጣት ምት) | 1 (4) | |||||||||||||
ሰኔ ፲፱ – ሩስተንበርግ | ||||||||||||||
ጋና | 1 (2) | |||||||||||||
አሜሪካ | 1 | |||||||||||||
ሰኔ ፳፱ – ኬፕ ታውን | ||||||||||||||
ጋና (በተጨማሪ ሰዓት) | 2 | |||||||||||||
ኡራጓይ | 2 | |||||||||||||
ሰኔ ፳፩ – ደርባን | ||||||||||||||
ኔዘርላንድስ | 3 | |||||||||||||
ኔዘርላንድስ | 2 | |||||||||||||
ሰኔ ፳፭ – ፖርት ኤልሳቤጥ | ||||||||||||||
ስሎቫኪያ | 1 | |||||||||||||
ኔዘርላንድስ | 2 | |||||||||||||
ሰኔ ፳፩ – ጆሃንስበርግ | ||||||||||||||
ብራዚል | 1 | |||||||||||||
ብራዚል | 3 | |||||||||||||
ሐምሌ ፬ – ጆሃንስበርግ | ||||||||||||||
ቺሌ | 0 | |||||||||||||
ኔዘርላንድስ | 0 | |||||||||||||
ሰኔ ፳ – ጆሃንስበርግ | ||||||||||||||
እስፓንያ (በተጨማሪ ሰዓት) |
1 | |||||||||||||
አርጀንቲና | 3 | |||||||||||||
ሰኔ ፳፮ – ኬፕ ታውን | ||||||||||||||
ሜክሲኮ | 1 | |||||||||||||
አርጀንቲና | 0 | |||||||||||||
ሰኔ ፳ – ብሉምፎንቴይን | ||||||||||||||
ጀርመን | 4 | |||||||||||||
ጀርመን | 4 | |||||||||||||
ሰኔ ፴ – ደርባን | ||||||||||||||
እንግሊዝ | 1 | |||||||||||||
ጀርመን | 0 | |||||||||||||
ሰኔ ፳፪ – ፕሪቶሪያ | ||||||||||||||
እስፓንያ | 1 | የደረጃ | ||||||||||||
ፓራጓይ (ቅጣት ምት) | 0 (5) | |||||||||||||
ሰኔ ፳፮ – ጆሃንስበርግ | ሐምሌ ፫ – ፖርት ኤልሳቤጥ | |||||||||||||
ጃፓን | 0 (3) | |||||||||||||
ፓራጓይ | 0 | ኡራጓይ | 2 | |||||||||||
ሰኔ ፳፪ – ኬፕ ታውን | ||||||||||||||
እስፓንያ | 1 | ጀርመን | 3 | |||||||||||
እስፓንያ | 1 | |||||||||||||
ፖርቱጋል | 0 | |||||||||||||
ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. 20፡30 |
ኔዘርላንድስ | 0 - 1 (በተጨማሪ ሰዓት) | እስፓንያ | ሶከር ሲቲ፣ ጆሃንስበርግ የተመልካች ቁጥር፦ 84,490 ዳኛ፦ ሀዋርድ ዌብ (እንግሊዝ) |
---|---|---|---|---|
ሪፖርት (እንግሊዝኛ) | አንድሬስ ኢኒየስታ 116' |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.