ወንጌል
From Wikipedia, the free encyclopedia
ወንጌል የሚለው ቃል (ከላቲን evangelium / ኢቫንጄሊየም, ይህም ራሱ ከጥንት የግሪክ ቃል εὐαγγέλιον / ኧውጄሊዮን = አስደሳች መልዕክት) ከሚለው የተገኘ ቃል ነው። ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ መልካም የምሥራች ነው፡፡ የንስሐ፣ የመፍትሄ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የተስፋ፣ የደኅንነት፣ የእርቅ፣ ከፍርድ የመዳን፣ የዘላለም ሕይወት፣ ትምህርት የሚገኝበት ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡
Quick Facts ወንጌል, የመዳኛ መልዕክት ...
Close
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር መንግስት አዋጅ የሆነውን ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ራሱ እንደሰበከ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል (ማቴ.፬፡፳፫፣ ማርቆ.፩፡፲፬-፲፭)፡፡ የወንጌል ዋነኛው መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። ሰዎች ከእግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ፤ኃጢአት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ማለት ከሁሉ የከፋውን ሞትን ለመሻር ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ እንደ ሰው ሆኖ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን በፈቃደኝንት ማለትም በሰላማዊ መንገድ አምኖ ማሳመን ነው (ሐዋ.፲፫፡፳፰-፴፣፴፰። ሮሜ.፫፡፳፭-፳፮፣ 1ቆሮ.፲፭፡፫-፬)።
በተለይ የዘላለማዊ ሕይወት ዕጣዬ ምንዓይነት ነው ለሚለው ጥያቄ ወንጌል ግልፅ የሆነ መልስ ይሰጣል።