እነብሴ ሳር ምድር
From Wikipedia, the free encyclopedia
እንብሴ ሳር ምድር በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው። ከታሪክ አንጻር፣ የእንብሴ ግዛት በ16ኛው ክፍለ ዘመን በተጻፈ መዝገብ ላይ ሰፍሮ ይገኛል [1] የዚህ ወረዳ አስተዳደር ማዕከል መርጡለ ማርያም ሲሆን ዲቦ የተሰኘው ከተማም ታዋቂ ነው። በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አሞኒዎስ እና የከንዳች ተጠቃሽ ናቸው። አባይ ወንዝ በበኩሉ ይህን ወረዳ ከሳይንት ወረዳ(ደቡብ ወሎ) ይለየዋል።
በ1994 ዓ.ም. በተደረገ ጥናት፣ የእርሻ መሬቱ በጣም ከመሸርሸሩ፣ ደኑ ከመጨፍጨፉ እና መሬቱ ከመግጠጡ አኳያ ወረዳው የምግብ እጥረት ካለባቸው ወረዳዎች ተርታ እንዲቀመጥ ሆኗል[2]።