![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/7/71/Young_wind_monitor.jpg/640px-Young_wind_monitor.jpg&w=640&q=50)
ነፋስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ነፋስ ሁለት አይነት ትርጉሞች አሉት። በመሬት ላይ፣ ንፋስ የሚባለው የአየር እንቅስቃሴ ነው። ከመሬት ውጭ ባለው ጠፈር ንፋስ የሚባለው የአየር ወይንም የተለያዩ እኑሶችን እንቅስቃሴ ነው። ለምሳሌ ከፀሐይ ፈንድተውና ተስፈናጥረው ወደ ጥልቁ ኅዋ የሚጓዙት እኑሶች ፀሐያዊ ነፋስን ይፈጥራሉ። በፀሐይ ሥርአተ ፈለክ(ፕላኔት) ውስጥ ከፍተኛ ነፋስ የሚነፍስባቸው ኔፕትዩንና ሳተርን ናቸው።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/7/71/Young_wind_monitor.jpg/640px-Young_wind_monitor.jpg)
ነፋስ እንደ ሃይሉና የሚውስደው ጊዜ እንዲሁም እንደ እርጥበቱ ይከፈላል፡፡ ከክፍሎቹም ውስጥ
- ለምለም ነፋስ- ቀስ ብሎ የሚነፍስ ነፋስ
- ልክስክስ ነፋስ - አቧራ ወደላይ አንስቶ ለትንሽ ደቂቃ ካንከባለለ በኋል በቶሎ የሚጠፋ
- ወዠብ ነፋስ - ዝናብ የሚቀላቅል ነፋስ
- አውሎ ነፋስ (ዊርል ዊንድ፣ ቶርኔዶ) - በኃይል እየተሽከረከረ የተለያዩ እቃዎችን ወደሰማይ እያጎና አደጋ የሚያደርስ