From Wikipedia, the free encyclopedia
ሮበርት ኔስታ ማርሊ (Robert "Bob" Nesta Marley; የካቲት 6 1945 - ግንቦት 11 1981 እ.ኤ.አ. ) በ1970ወቹ እና 80ወቹ ከፍተኛ እውቅናን ያገኘ ግን እስካሁን ድረስ ተወዳጅነቱ የቀጠለ የጃማይካ አገር ዘፋኝ ነበር። የሬጌን ሙዚቃ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እንዲሆን ያደረገ ዋና ሙዚቀኛ ነበር። ዘፈኖቹ ባጠቃላይ መልኩ ስለ ጃማይካ ኑሮ የሚተርኩና ስለ ራስ ተፈሪያን ሃይማኖት የሚያትቱ ነበር። በሌላ አነጋገር ዘፈኖቹ ስለፍቅር ከመተረክ ይልቅ ወደ ፖለቲካና ወደ ሃይማኖት ያጋደሉ ነበር።
ቦብ ማርሊ እናቱ ሴዴላ ቡከር የምትባል ጥቁር ጃማይካዊት ስትሆን አባቱ ደግሞ ኖርቫል ማርሊ የተባለ ነጭ እንግሊዛዊ ነበር። የሙዚቃ ሕይወቱንም የጀመረው በ1960ወቹ ፒተር ቶሽ እና በኒ ዌይለር ከተባሉ ጓደኞቹ ጋር ዘ ዌይለርስ የተባለ ቡድን በመመስረት ነበር። ከዚያም ከደጋፊ ዘፋኞቹ አንዲቱ የነበረችውን ሪታ ማርሊን በማግባት 5 ልጆች አፍርቷል። ከነዚህ ውስጥ አንዱ ዚጊ ማርሊ፣ በራሱ የተዋጣለት የሬጌ ዘፈን ተጫዋች ነው። ከቦብ ማርሊ ታላቁ የሙዚቃ ስራ ኖ ውማን ኖ ክራይ ወይም ቃል በቃል ሲተረጎም «አይ ሴትዬ አታልቅሽ» የሚለው ነበር[1]። በርግጥም ሮበርት ኔስታ ማርሊ በአገሩ በጃማይካ እንደ ታላቅ ጀግና የሚቆጠር ሰው ነው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.