ሸሺ መዓይብሬ ግብጽን በ፪ኛው ጨለማ ዘመን (14ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1786 እስከ 1753 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

==

Quick Facts ሸሺ መዓይብሬ, ግዛት ...
ሸሺ መዓይብሬ
«ሳ-ሬ ሸሺ ጁ አንኽ» (የሬ ልጅ ሸሺ ይኑር) በጢንዚዛ ማኅተም ላይ እንደ ተጻፈ
«ሳ-ሬ ሸሺ ጁ አንኽ» (የሬ ልጅ ሸሺ ይኑር) በጢንዚዛ ማኅተም ላይ እንደ ተጻፈ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1786-1753 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ አሙ አሆተፕሬ
ተከታይ ነህሲ
ባለቤት ታቲ
ሥርወ-መንግሥት 14ኛው ሥርወ መንግሥት
Close

==

የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልትሥነ ቅርስ እንደሚያስረዳው፣ ከአሙ አሆተፕሬ ቀጥሎ ሸሺ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለጤቤስ ፈርዖኖች ተገዥ ሆኖ ነገሠ። ሕዝቡ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ።

በርካታ (300 ያህል) የ«ሸሺ» ወይም የ«መዓይብሬ» ጢንዚዞች በዚያ ወቅት በዙሪያው እንደ ገዛ ይገልጻሉ፤ እነዚህም ስያሜዎች አብረው ባይታዩም ለአንዱ ፈርዖን መሆናቸው ይታስባል። ከነዚህ ቅርሶች ጥቂቶች በከነዓን፣ በአቢዶስ ወይም በኩሽ መንግሥት (ሰምና) በመገኘታቸው የንግድ ተቀባዮቹን ያመልክታል።[1] የሸሺ ንግሥት ስም «ታቲ» ሲሆን በራይሆልት ዘንድ ይህ የኩሻዊት ስም ይመስላል፤ የልጁም ነህሲ ስም ማለት «ኩሻዊ» ስለሆነ፣ እናቱ ታቲ ኩሻዊት ልዕልት መሆኗን ያስባል።

ሆኖም በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ፣ ሸሺ በኋላ በ15ኛው ሥርወ መንግሥት (የሂክሶስ) ውስጥ ነበር የነገሠ።


ቀዳሚው
(አሙ አሆተፕሬ)
አባይ ወንዝ አፍ (ጌሤም) ፈርዖን ተከታይ
ነህሲ
  1. Kim Ryholt, 1997, The Political Situation in Egypt During the Second Intermediate Period p. 365.

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.