From Wikipedia, the free encyclopedia
አሙ አሆተፕሬ ግብጽን በ፪ኛው ጨለማ ዘመን (14ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1791 እስከ 1786 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
==
==
የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት ከሥነ ቅርስ እንደሚያስረዳው፣ ከቃረህ ኻዎሰሬ ቀጥሎ አሙ አሆተፕሬ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለጤቤስ ፈርዖኖች ተገዥ ሆኖ ነገሠ። ሕዝቡ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ።
አያሌ (60 ያህል) የ«አሙ» ወይም የ«አሆተፕሬ» ጢንዚዞች በዚያ ወቅት በዙሪያው እንደ ገዛ ይገልጻሉ፤ እነዚህም ስያሜዎች አብረው ባይታዩም ለአንዱ ፈርዖን መሆናቸው ይታስባል። ከነዚህ ቅርሶች ጥቂቶች በከነዓን፣ በአቢዶስ ወይም በኩሽ መንግሥት (ሰምና) በመገኘታቸው የንግድ ተቀባዮቹን ያመልክታል።[1] ሆኖም በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ፣ አሆተፕሬ በኋላ በ16ኛው ሥርወ መንግሥት ውስጥ ነበር የነገሠ።
ቀዳሚው (ቃረህ ኻዎሰሬ) |
የአባይ ወንዝ አፍ (ጌሤም) ፈርዖን | ተከታይ ሸሺ ማዓይብሬ |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.