ሮድኢ
From Wikipedia, the free encyclopedia
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሮድኢ (ዕብራይስጥ፦ דודנים /ዶዳኒም/ ወይም רודנים /ሮዳኒም/፤ ግሪክኛ፦ Ρόδιοι /ሮዲዮይ/) በኦሪት ዘፍጥረት 10:4 ፩ ዜና መዋዕል 1:7 መሠረት የያዋን ያፌት ፬ኛ ልጅ ነበር።
በሳምራዊው ትርጉምና በአንዳንድ ዕብራይስጥ ቅጂ ስሙ ሮዳኒም ተጽፎ መታወቂያው የሩድ (ግሪክኛ፦ ሮዶስ) ደሴት ሰዎች አባት እንደ ነበር ይገመታል።[1] እንዲሁም በግሪክኛው ትርጉም ሮዲዮይ ሲባል ይህም ማለት የሩድ ሰዎች ሊሆን ይችላል። በዕብራይስጥም ይህ «ሮዳኒም» የያዋን ልጅ ስም ቢሆንም «-ኢም» የሚለው መድረሻ ብዙ ጊዜ ለብዙ ቁጥር (ለብሔር ስም) ይጠቀማል። በሌላ አስተሳሰብ ፈረንሳያዊው ምሁር ሳሙኤል ቦሻር «ሮዳኒም» በደቡብ ፈረንሳይ ካለው ከሮን ወንዝ (በጥንት፦ «ሮዳኑስ ወንዝ») ስም ጋር ግንኙነት እንደ ነበር አሰቡ።
በሌላ በኩል ዶዳኒም የሚለው አጻጻፍ በብዙዎች ቅጂዎች በመገኘቱ፣ ግንኙነት ከዶዶና በኤጲሮስ (ስሜን-ሜራብ ግሪክ እና አልባኒያ) ወይም ደግሞ ከዳርዳኒያ (የዛሬው ኮሶቮ አካባቢ) ጋር እንዳለው ታስቧል። እነዚህ አገሮች በግሪኮችና በእልዋሪቆን መካከል ነበሩ። ዳርዳኖይ የሚባል ብሔር በሆሜር ዘንድ በትሮአስ ወገን ተዋጉ። በግብጽም መዝገቦች «ዳርዳናዩ» የተባለ ግሪካዊ ብሔር በ፫ አመንሆተፕ ዘመን (1394-1355 አክልበ.) ሲጠቀስ፤ በኋላ ደግሞ በቃዴሽ ውግያ (1283 ዓክልበ.) «ዳኑኒም» የተባለ ጎሣ በኬጢያውያን ወገን ተዋጉ። እነዚህ ሕዝቦች ምናልባት ከ«ዶዳኒም» ጋር አንድላይ እንደ ሆኑ የሚያስቡ ደራስያን አሉ።[2]
በ62 ዓ.ም. ግድም የተጻፈው አይሁዳዊ መጽሐፍ «የመጽሐፍ ቅዱስ ቅርሶች» (ሐሣዊ-ፊሎ የተባለው መጽሐፍ) እንደሚለው፣ ስሙ ድዎደኒም ተብሎ ልጆቹ ኢጤብ፣ በዓጥ እና ፌኔክ ይባላሉ። ይህ መጨረሻ ልጅ ፌኔክ በባቢሎን ግንብ ወቅት የያፌት ልጆች አለቃ ሆነ (ናምሩድና ዮቅጣን ለካምና ሴም ልጆች አለቆች ሲሆኑ ነው)።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.