ሙሴ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሙሴ (ዕብራይስጥ፡ מֹשֶׁה /ሞሼህ/) በብሉይ ኪዳን ከሚጠቀሱት ታላላቅ ነብያት አንዱ ነው። ሙሴ በተወለደበት ዘመን የእስራኤል ልጆች በግብጽ ውስጥ በባርነት ተገዝተው የነበርበት ሆኖም ግን ቁጥራቸው እየበዛና እየተጠናከሩ የነበርበት ጊዜ ነበር።
Quick Facts ታላቁ ነብይ ሙሴ, ነፃ አውጪው ...
ታላቁ ነብይ ሙሴ | |
---|---|
ነፃ አውጪው | |
የኖረበት ዘመን | ሺ፬፻ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት |
ዜግነቱ | እስራኤላዊ |
ያደገው | በግብፅ ፈርዖን ቤት |
የአባት ስም | አንበረም |
የእናት ስም | ዮካብድ |
ወንድምና እህቱ | አሮንና ማርያም |
የባለቤቱ ስም | ሲፓራ |
የሚከበረው | በአይሁድና ፣ በክርስትና ፣ በእስልምና ሃይማኖቶች እምነት ተከታዮች |
በዓል ንግሥ | የካቲት ፲፯ |
Close
በዚህ ዘመን ግብፅን ያስተዳድር የነበር፣ ስሙ በብሉይ ኪዳን ያልተጠቀሰው የግብፅ ፈርዖን፣ የእስራኤል ልጆች ከውጭ የግብፅ ጠላቶች አግዘው ሊወጉን ይችሉ ይሆናል በሚል ፍራቻ ማናቸው የእስራኤል ወገን የሆኑ ወንድ ልጆች በተወለዱ ጊዜ እንዲገደሉ አዘዘ። ሆኖም የሙሴ እናት፣ ዮካብድ፣ ልጇን ደብቃ ታኖር ነበር። ከሶስት ወር ድበቃ በኋላ ልጁን በደንገል ሳጥን አድርጋ በአባይ (ናይል) ወንዝ አጠገብ አስቀመጠችው። ሳጥኑ እየተንሳፈፈ የፈርዖን ልጅ እምትታጠብበት ስፍራ ደረሰ፣ የፈርዖንም ልጅ ለህጻኑ ስላዘነች በፈርዖን ቤት አደገ።