ፈርዖን ማለት የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ነው። ይህ ከግብጽኛ «ፐር-ዓ» ከ«ፐር» (ቤት) እና «ዓ» (ታላቅ) ወይም «ታላቁ ቤት» ደረሰ። ፐር-ዓ መጀመርያ ቤተ መንግሥት ለማመልከት ሲሆን፣ ከ1400 ዓክልበ. በኋላ ንጉሡን ፐር-ዓ ይሉት ጀመር። ስለዚህ ከዚያ በፊትም የነገሡት ግብጻዊ ንገሥታት ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረትአብርሐም፣ በዮሴፍ ወይም በሙሴ ዘመን የነበሩት ነገሥታት ደግሞ «ፈርዖን» ተብለዋል። ነገር ግን በታሪክ ላይ ፈርዖን የሚለው ማዕረግ ጥቅም ላይ የዋለው በጥንቱ የግብጽ መንግሥት ከ 2691-2625 ሳይሆን አሊያም በመካከለኛው የግብጽ መንግሥት ከ 2050-1710 ሳይሆን በአዲሱ የግብጽ መንግሥት በ 1570 ነው። ቁርኣንም ፈርዖን ማለት የጀመረበት በአዲሱ የግብፅ መንግሥት በሙሴ ዘመን ነው።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.