From Wikipedia, the free encyclopedia
ሉክሰምበርግ: በኅዳር ፪፻፮ ዓ/ም ዛቪዬ በተል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኑ ሉክሳምቡርግ ከቤልጅግና አይስላንድ በኋላ ሦስተኛው ሰዶማዊ የመንግሥት መሪ ያለው አገር ሆነ። በይፋ ሉክሰምበርግ በምእራብ አውሮፓ የምትገኝ በመሬት ተከበበች ሀገር ናት፡፡ በምእራብ እና ሰሜን ከቤልጂየም፣ በምስራቅ ከጀርመን፣ እና በደቡብ ከፈረንሳይ ጋራ ትዋሰናለች፡፡ መዲናዋ ሉክምበርግ ሲቲ ከብሩሰልስ እና ስትራስቦርግ ጋር የአውሮፓ ህብረት፣ የምስራቅ አውሮፓ የፍትህ ፍርድ ቤት፣ የኢዩ ከፍተኛ የህግ አውጪ ባለስልጣን መቀመጫዎች ናቸው፡፡ ባሕሏ፣ ህዝቦቿ እና ቋንቋዋ በከፍተኛ ሁኔታ ከአጎራባች ሐገራት ጋራ በመወራረሱ የተነሳ በዋነኛነት የፈረንሳይ እና የጀርመን ባሕሎች ቅይጥ ሐገር ሆናለች፡፡ ይሄም በሐገሪቱ በሚነገሩ ሶስት አበይት ቋንቋዎች ጉልህ ሆኖ ይቀርባል እነዚህም ሉክሰምበርጊሽ፣ ፈረንሳይኛ፣ እና ጀርመንኛ ናቸው፡፡ በአጎራባች ሐገራት በተለይም በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ተደጋግሞ የደረሰባት ወረራ የተነሳ ሐገሪቱ በፈረንሳይ እና ጀርመን ድርድር ፈቋዷ እንዲወሰን የሆነ ሲሆን ከብዙ በጥቂቱ የአውሮፓ ሕብረት እንዲመሰረት መሰረቱን ጥሏል፡፡
Groussherzogtum Lëtzebuerg |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: "Ons Heemecht" |
||||||
ዋና ከተማ | ሉክሰምበርግ (ከተማ) | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ሉክሰምበርግኛ | |||||
መንግሥት {{{ንጉስ ጠቅላይ ሚኒስትር |
አንሪ አልበር ጋብሪየል ፌሊ ማሪ ጊዮም ዛቭዬ ቤተል |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
2,586.4 (168ኛ) |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት |
576,249 (20ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ዩሮ (€) | |||||
የስልክ መግቢያ | +352 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .lu |
ስፋቷ 2,586 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ሲሆን (998 ስኩ.ማይልስ) በአውሮፓ ውስጥ ካሉ ሉዐላዊ ሐገራት ውስጥ ትን ግዛት ስትሆን የዩኤስ የሮዴ ደሴትን ያህል ስፋት ወይም የእንግሊዟን ኖርዛምፕተንሻየር ታህላለች፡፡ በ2016 በአውሮፓ ውስጥ በእጅጉ ዝቅተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ሐገር የሚያደርጋት 576,429 ህዝብ ያላት ሲሆን ነገር ግን እስካሁን ከፍተኛው የህዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔ ያላት ሐገር ናት፡፡ በህገመንግስታዊ የዘውድ ስርዐት የተወካይ ዴሞክራሲ እነደመኖሩ በከፍተኛው የሉክሰምበርግ መስፍን ከፍተኛ መስፍን ሄነሪ የምትመራ ሲሆን በአለማችን ላይ በመሳፍንት አገዛዛ ስር ያለች ብቸኛ ቀሪዋ ሐገር ናት፡፡ እንደተባበሩት መንግስታት የ2014 መግለጫ ከሆነ ሉክሰምበርግ ያደገች ሐገር ስትሆን ኢኮኖሚዋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በአለማችንም ከፍተኛው የነፍስ ወከፍ ምጣኔ ሐብት ያላት ሐገር ናት፡፡ የሉክሰምብግ ሲቲ እድሜ ጠገብ የከተማ ክፍሎቿ እና ምሽጎቿ በ1994 ከፍተኛ ምሽጎችን እና እድሜ ጠገብ ከተማ በልዩ ብቃት ጠብቃ በማቆየቷ የዩኔስኮ የአለም ቅርስ በመሆን ተመዝግባለች፡፡
የሉክሰምበርግ ታሪክ ጀምሯ ተብሎ የሚታሰበው በ963 ባላበት ሲግፍሬድ I ባሕረ ሰላጤውን ኮረብታማ መሬት ሲወስድ እና ሉሲሊንቡርሁክ፣ “ትንሽ ግንብ” በመባል የሚታወቀውን የሮማውያን ዘመን ምሽግ፣ እና አካባቢው በቅርቡ ከሚገኘው የንጉሳዊ የቅይዱስ ማክሲሚን ገዳም ከወሰደ በኋላ ጀምሯል፡፡ የሴግፍሬድ ዘሮች ግዛታቸውን በጋብቻ፣ በጦርነት እና በጭሰኛ እና ጌታ ግንኙነት አስፋፍተውታል፡፡ የሉክሰምርግ ባላባቶች በ13ኛው ክፍለዘመን ፍፃሜ ላይ ከፍተኛ ግዛት ላይ መንሰራፋት እና መግዛት ችለዋል፡፡ በ1308 የሉክሰምበርግ ባላባት የሆነው ሄነሪ VII የጀርመኖች እና የቅዱስ ሮማውያን ንጉሰ ነገስት ንጉስ ሆነ፡፡ የሉክሰምበርግ ተወካዮች ምክር ቤት በመካከለኛው ዘመን አራት ቅዱስ የሮማውያን ንጉሰ ነገስቶችን ሾሟል፡፡ በ1354 ቻርልስ IV መስተዳድሩን ወደ መሳፍንት ሉክሰምበርግ ቀይሮታል፡፡ ሲጊስሙንድ ወንድ ወራሽ ስላልነበረው መሳፍንቱ ከቡርጉንዲያን በከፊል ሆነዋል እንዲሁም የሐብስቡርግ፣ ኔዘርላንድስ አስራሰባት ግዛተቶች መካከል ሆኗል፡፡ ባለፉት ምዕተ አመታት በፈረንሳይ ንጉሳዊ መንግስት እና በሐብስቡርግ ግዛቶች መካከል የሚገኙት ከፍተኛ ስትራቴጂክ አስፈላጊነት ያላቸው የሉክሰምበርግ ከተማ እና ምሽጎቿ በአውሮፓ ውስጥ በእጅጉ ዝናን ካተረፉ ምሽጎች አንዱ ለመሆን እንዲችሉ ተደርገው የተገነቡ ናቸው፡፡ የፈረንሳዩ ሉዊስ XIV እና የኦስትሪያዋ ማሪያ ቴሬዛ ከተቆጣጠሯት በኋላ ሉክሰምበርግ የመጀመሪያው የፈረንሳይ ሪፐብሊክ እና በናፖሊዎን ስር የነበረው ንጉሳዊ አገዛዝ አካል ሆናለች፡፡
የአሁኗ ሉክሰምበርግ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሐገር ብቅ ያለችው በ1815 በቪዬና ኮንግረስ ወቅት ነበር፡፡ ከሐይለኛ ምሽጎቹ ጋር ከፍተኛው መስፍን ከተማዋን በፈረንሳይ ከሚሰነዘርባት ሌላ ወረራ ለመከላከል ከፕሩሲያን ሽምቅ ተዋጊዎች ጋራ በኔዘርላንድሱ ዊሊያም I የግል ቁጥጥር ስር በመሆን ነጻ እና ገለልተኛ ሐገር ሆናለች፡፡ በ1839 ከቤልጂየም አብዮት መፈንዳት በኋላ ፈረንሳይኛ ብቻ የሚናገረው የሰሉክሰምበርግ አካል ወደቤልጂየም ተቀላቅሏል እና ሉክሰምበርጊሽ ተናጋሪው ክፍል የአሁኗን ሉክምሰምበርግ መስርተዋታል፡፡
በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የቀዩን ምድር የበለፀገ ብረታዘል መሬት የብረት ኢንዱስትሪው ፍለጋ ባደረገበት ወቅት ሐገሪቱን ወደኢንዱስትሪ ግስጋሴ ውስጥ አስገብቷቷል፡፡ ዋና መስሪያ ቤቱን በሉክሰምበርግ ከተማ ያደረገው የአለማችን ታላቁ የብረት አምራች የሆነው አርሴሎርሚታል አሁንም እነዚህን ወቅቶች የሚያስታውሰን ነው፡፡ በ1960ዎቹ የብረት ኢንዱስትሪው ውድቀት ካስመዘገበ በኋላ የአለማችን የገንዘብ ማዕከል ፣ለመሆን ሐገሪቱ ራሷን በማደራጀቱ ላይ ትኩረቷን በማድረግ አሁን የታወቀችበትን የባንክ ማዕከል ለመገንባት ችላለች፡፡ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጅማሬ አንስቶ መንግስቶቿ ሐገሪቱን በእውቀት ወደታነጸ ኢኮኖሚ ልማት ውስጥ በማስገባቱ ላይ ያተከረች ሲሆን ከዚህም ጋራ ተያይዞ የሉሰምበርግ ዩንቨርስቲ እና ብሔራዊ የህዋ ፕሮግራም በ2020 ወደጨረቃ በሚደረግ ሰው አልባ ጉዞ ላይ የመጀመሪያ ተሳትፎዋን ለማድረግ በማቀድ መስርታለች፡፡ ሉክሰምበርግ የአውሮፓ ህብረት፣ ኦኢሲዲ፣ የተባበሩት መንግስታት፣ ናቶ፣ እና ቤኔሉክስ መስራች አባል ስትሆን የፖለቲካ ስምምነቷን በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ውህደት ላይ መስርታለች፡፡ የሐገሪቱ መዲና እና ትልቋ ከተማ የሆነችው የሉክሰምበርግ ሲቲ የአውሮፓ ህብረት በርካታ ተቋማት እና ኤጀንሲዎች መቀመጫ ናት፡፡ የሐገሪቱ የመጀመሪያው ታሪክ ሆኖ በተመዘገበው ሉክሰምበርግ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በ2005 እና 2006 አገልግላለች፡፡ በ2016 የሉክሰምበርግ ዜጎች ወደ 172 ሐገራት እና ግዛቶች ነጻ ቪዛ ወይም በደረሱበት ቪዛ እንዲሰጣቸው ሆኖ የነበረ ሲሆን ካናዳ እና ስዊትዘርላንድ ከመሳሰሉ ሐገራት ጋራ በተያያዘ የሉክሰምበርጋዊን ፓስፖርት በአለም 6ኛው በመሆን ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡
ማውጫዎች
1. ታሪክ · 1.1 ሐገር · 1.2 መሳፍንት · 1.3 አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን · 1.4 ሐያኛው ክፍለ ዘመን 2. ፖለቲካ · 2.1 አስተዳደራዊ መምሪያዎች · 2.2 የውጭ ግንኙነት · 2.3 ወታደር 3. መልክዐ ምድር · 3.1 አየር ንብረት 4. ኢኮኖሚ · 4.1 ትራንስፖርት · 4.2 ግንኙነቶች · 4.3 የዳታ ማዕከላት 5. የእነ-ህዝብ መረጃ · 5.1 ዘር · 5.2 ቋንቋ · 5.3 ሐይማኖት · 5.4 ትምህርት · 5.5 ጤና 6. ባሕል · 6.1 ስፖርት · 6.2 ምግብ · 6.3 ሚዲያ 7. በተጨማሪም ይመልከቱ |
ታሪክ
ሐገር
የሉክሰምበርግ ታሪክ መመዝገብ የጀመረው በሲግፍሪድ፣በአርዴኔስ ኮርት የሚገኘው እድሜ ጠገብ ቋጥኝ ያለው ሉሲሊንቡሩህክ (የዛሬው የሉክሰምበርግ የንጉሳዊያን መኖሪያ) በመያዝ፣ የንጉሳዊው የቅይዱስ ማክሲሚን ገዳም ልውውጥ በ1955 እ.ኤ.አ. በማድረግ ነው፡፡ በዚህ ምሽግ አካባቢ ከተማ በሂደት መመስረቱን በመቀጠል ከፍተኛ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ያለው ማዕከል መሆን ችሏል፡፡
የመሳፍንት ግዛት
በ14ኛው እና 15ኛው ክፍለ ዘመናት ሶስት የሉክሰምበርግ ምክር ቤት አባላት የሮማ ቅዱሳት ነገስታት በመሆን ነገሱ፡፡ በ1437 እ.ኤ.አ. የሉክሰምበርግ ምክር ቤት በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ወንድ በማጣት የአልጋ ወራሽ ችግር ገጥሞት ነበር፣ ይኸውም ግዛቶች በደቿ ኤልሳቤጥ ለቡርገንዲው ፊሊፕ እንዲሸጥ አድርጓል፡፡
በሚከተሉት ምዕተ አመቶች የሉክምበርግ ምሽግ ተከታትለው በመጡ ሰፋሪዎቿ፣ ቦርቦኖች፣ ሐብስበርጎች፣ ሆሄንዞለርንስ እና ፈረንሳዮች ከጊዜ ወደጊዜ ሰፍቷል እንዲሁም ተጠናክሯል፡፡
አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን
ናፖሊዎን በ1815 እ.ኤ.አ. ከተሸነፈ በኋላ፣ ሉክሰምበርግ በፕሩሺያ እና በኔዛርላንድስ መካከል ክርክር እንዲፈጠርባት ምክንያት ሆናለች፡፡ ከኔዘርላንድስ ጋራ በሕብረት በመሆን በጀርመን ኮንፌዴሬሽን ውስጥ የቪዬና ኮንግረስ ሉክሰምበርግን እንደትልቅ መሳፍንት አመራር በማድረግ የመሰረታት ሲሆን፣ በዚሁ ጊዜ የኔዘርለንድስ አካል በመሆን እና እንደአንድ ግዛቷ በመሆን እየተመራች የሉክሰምበርግ ምሽጎች በፕሩሺያ ጦር ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ይሄ ስምምነት በለንደኑ የ1839 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያው ስምምነት የተከለሰ ሲሆን ከዚሁ እለት በኋላ የሉክሰምበርግ ሙሉ ነጻነት ከ1830-1839 እ.ኤ.አ. የቤልጂየም አብዮት በተነሳበት ወቅት ዕውን የሆነ ሲሆን እና በ1839 እ.ኤ.አ. ስምምነት ሙኑ ነፃነቷን ተቀዳጅታለች፣ የሉክሰምበርግ ግዛት ከግማሽ በላይ የተቀነሰ ሲሆን፣ በብዛት የፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆነው ምዕራባዊው የሐገሪቱ ክፍል ወደቤልጂየም ተዛውሯል፡፡ በ1842 እ.ኤ.አ. ሉክሰምበርግ የጀርመንን የጉምሩክ ሕብረት (ዞልቨሬይን) ተቀላቅላለች፡፡ ይኸውም የጀርመን ገበያ እንዲከፈት፣ የሉክሰምበርግ የብረት ኢንዱስትሪ እንዲያድግ፣ እና የሉክሰምበርግ የምድር ባቡር ኔትወርክ ከ1855 እስከ 1875 እ.ኤ.አ. ድረስ እንዲስፋፋ፣ በተለይም ከዚህ አንስቶ የአውሮፓውያንን የኢንዱስትሪ ክልሎች የሚያገናኘው የሉክሰምበርግ-ቲዎንቪል የባቡር ሐዲድ እንዲገነባ አድርጓል፡፡ አሁንም የፕሩሺያ የጦር ሰራዊት ምሽጎቹን ተቆጣጥረዋቸው ስለነበር በ1861 እ.ኤ.አ. ፓሰሬል ተከፈተ፣ ቪል ሆትን እና በቦክ የሚገኙትን ዋና ምሽጎች ከሉክሰምበርግ የምድር ባቡር ጣቢያ ጋር የሚያገናኘው የፔትሩስ ወንዝ ሸለቆን የሚያቋርጠው የመጀመሪያው የመንገድ ላይ ድልድይ፤በደቡብ አቅጣጫ በሚገኘው በዚያ ወቅት በተመሸገው ቡርቦን ሜዳማ ክፍል ላይ በ1959 እ.ኤ.አ. ተከፈተ፡፡
በ1866 ከተከሰተው የሉክሰምበርግ ችግር በኋላ በፕሩሺያ እና ፈረንሳይ መካከል ጦርነት የተፈጠረ ሲሆን፣ ከፍተኛው የመሳፍንት ነጻነት እና ገለልተኝነት በ1867ቱ እ.ኤ.አ. በለንደኑ ሁለተኛው ስምምነት በድጋሚ ተረጋግጧል፣ የፕሩሺያ የጦር ሰራዊት ከሉክሰምበርግ ምሽጎች በመውጣት ቦክ እና በአቅራቢያው የሚገኙ ምሽጎች ፈራርሰዋል፡፡
የኔዘርላንድስ ንጉስ የሉክሰምበርክ ከፍተኛ መስፍን ርዕሰ ብሔር በመሆን የቀጠለ ሲሆን፣ እስከ 1890 እ.ኤ.አ. ድረስ በሁለቱ ሐገራት መካከል ያለውን የሁለቱን ሐገራት ግንኙነት አስቀጥሏል፡፡ ዊሊያም III ከዚህ አለም በሞት ሲለይ የኔዘርላንድስ ዙፋን ወደሴት ልጁ ዊልሔልሚና ተላለፈ፣ በዚህም ሁኔታ ሉክሰምበርግ (በናሱ ቤተሰብ ፓክት በወንድ ወራሾች ብቻ ተወስኖ የነበረው) ወደናሱ-ዌይልበርጉ አዶልፍ ተላልፏል፡፡
በ1870 እ.ኤ.አ. በፍራንኮ-ፕሩሺያን ጦርነት ጊዜ ወታደሮችን ከሜትዝ (በመቀጠል ጠፈረንሳይ ክፍል የሆነችው) በመሳፍንቱ ሐገር እንዲያልፉ ፈረንሳይ የባቡር ሐዲዱን መጠቀሟን አስመልክተቶ እና ወደቲዎንቪል አቅርቦቶችን ለማቅረብ ምንም እንኳን ክርክሮች የነበሩ ቢሆንም፣ የሉክሰምበርግ ገለልተኛነት በጀርመን አክብሮት ተቸሮታል፣ እና ጀርመንም ሆነች ፈረንሳይ ሀገሪቱን ወረዋት አያውቁም፡፡ ነገር ግን በ1871እ.ኤ.አ. ጀርመን በፈረንሳይ ላይ ድል በመቀዳጀቷ ሜትዝ እና ቲዎንቪልን ጨምሮ ሉክሰምበርግ ከሎሬን ጋራ ያላት ድንበር ከፈረንሳይ ጋራ ከመጎራበት ይልቅ በፍራክፈርት ስምምነት መሰረት እንደአልሴስ-ሎሬን ከጀርመን ንጉሳዊ መንግስት ጋራ ወደተያያዘችው ተለውጧል፡፡ ይሄም ጀርመን የባቡር ሐዲዶችን የመቆጣጠር እና የማስፋፋት ወታደራዊ ጥቅም እንድታገኝ አስችሏታል፡፡
ሐያኛው ክፍለ ዘመን
ኦገስት 1914 እ.ኤ.አ. ንጉሳዊቷ ጀርመን ከፈረንሳይ ጋራ ባደረገችው ጦርነት በሉክሰምበርግ ላይ ወረራ በማካሄድ የሉክሰምበርግን ገለልተኝነት ጥሳለች፡፡ ይሄ ሁኔታ ጀርመን የባቡር ሐዲዱን መጠቀም እንድትችል አድርጓቷል፡፡ በዚሁ ሁኔታ ከፈረንሳይ ነጥቃዋለች፡፡ ይሁንና ከጀርመን ሰፈራ ባሻገር ሉክሰምበርግ አብዛኛውን ነጻነቷን እና የፖለቲካ ስልቶቿን እንድታስቀጥል ሁኔታዎች ተመቻችተውላታል፡፡
በ1940 እ.ኤ.አ. የII ኛው የአለም ጦርነት ከተነሳ በኋላ የናዚ ጀርመን ዌህርማችት ወደሐገሰሪቱ በገባ ጊዜ የሉክሰምበርግ ገለልተኛነት በድጋሚ “ሙሉ ለሙሉ ያለማብራሪያ” ተጣሰ፡፡ ከመጀመሪያው የአለም ጦርነት በተቃርኖ በሆነ መንገድ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ጀርመን በሉክሰምበርግ መስፈሯ ሐገሪቱን የጀርመን ግዛት ተደርጋ እንድትቆጠር አድርጓታል እና ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ በትይዩ ከምትገኘው ከሶስተኛዋ ሬይች አውራጃ ጋር እንድትያያዝ አድርጓታል፡፡ መቀመጫውን በለንደን አድርጎ የነበረው በስደት ላይ የነበረው መንግስት አጋሮችን በመደገፍ በኖርማንዲ ወረራ ላይ ተሳታፊ የሆኑ በጎ ፈቃደኛ አናሳ ቡድኖችን ልኮ ነበር፡፡ ሉክሰምበርግ በሴፕቴምበር 1944 እ.ኤ.አ. ነጻ የወጣች ሲሆን በ1945 እ.ኤ.አ. የተባበሩት መንግስታት መስራች አባል ሆናለች፡፡ በህገመንግስቱ የሉክሰምበርግ ገለልተኛ አቋም በ1948 ያበቃ ሲሆን በ1949 እ.ኤ.አ. የናቶ መስራች አባል ሐገር ሆናለች፡፡
በ1951 ከስድስቱ የአውሮፓውያን የድንጋይ ከሰል እና የብረት ማሕበረሰብ አንዷ የሆነች ሲሆን ይኸውም ማሕበረሰብ በ1957 እ.ኤ.አ. የአውሮፓውያን የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ የሆነው እና በ1993 እ.ኤ.አ. የአውሮፓ ሕብረት የሆነው ሕብረት ሲሆን እንዲሁም በ1999 እ.ኤ.አ. ሉክሰምበርግ የዩሮ መገበያያ አካባቢን ተቀላቅላለች፡፡ በ2005 እ.ኤ.አ. ለአውሮፓ ህገመንግስት በሚመሰርተው የአሕ ስምምነት ላይ ህዝበ ውሳኔ ተካሂዷል፡፡
ፖለቲካ
ሉክሰምበርግ በህገመንግስታዊ የዘውድ አገዛዝ የሚመራ የፓርላማ ዲሞክራሲ ያላት ሐገር ናት፡፡በ1868ቱ እ.ኤ.አ. ህገመንግስት የህግ አስፈጻሚነት ስልጣን በከፍተኛው መስፍን እና በርካታ ሌሎች ሚኒስቴሮችን በያዘው ካቢኔው ተይዞ ነበር፡፡ ከፍተኛው መስፍን የህግ ረቂቅን የማፍረስ አቅም የነበረው ሲሆን በዚህ ሁኔታ አዲስ ምርጫ በሶስት ወራት ጊዜ መከናወን ነበረበት፡፡ ይሁንና ከ1919 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሐገሪቷ ሉዐላዊነት ሰፈነ፣ በህገመንግስቱ እና በህጉ መሰረት በከፍተኛ መስፍኑ ይተገበራል፡፡
የህግ ማውጣት ስልጣን ለዲኤታው ምክር ቤት፣ ከአራት የመራጮች አካላት ለአምስት አመት የስልጣን ዘመን ለተመረጡ ስልሳ አባላት ላሉት በአንድ የህግ አውጭው አካል ለተዋቀረው የህግ አውጪ ተሰጥቷል፡፡ ሁለተኛው አካል፣ የሐገሪቱ ምክር ቤት (ኮንሴይል ድኢታት) በከፍተኛው መስፍን የተመረጡ ሐያ አንድ መደበኛ ዜጎችን የያዘ ሲሆን የህግ ረቂቆችን በማርቀቁ ሂደት የዲኤታዎችን ምክር ቤት ያማክራል፡፡
ከፍተኛው መስፍን ሶስት የስር ፍርድ ቤቶች ያሉት ሲሆን (ጀስቲስ ደ ፔይክስ፣ በኢስች-ሱር-አልዜቴ፣ የሉክሰምበርግ ከተማ እና ዲየኪርች)፣ ሁለት አውራጃ ፍርድ ቤቶች (ሉክሰምበርግ እና ዲየኪርች) እና የፍትህ ከፍተኛ ፍርድ ቤት (ሉክሰምበርግ)፣የአቤቱታ ፍርድ ቤቱን እና የሰበር ሰሚ ችሎትን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም አስደተዳደራዊ ችሎት እና አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ያለ ሲሆን እንዲሁም የህገመንግስቱ ፍድ ቤት ሁሉም በመዲናዋ ይገኛሉ፡፡
አስተዳደራዊ መምሪያዎች
ሉክሰምበርግ በ12 የአስተዳደር ክፍሎች የተከፈለች ሲሆን በ105 ትንንሽ የአስተዳደር ክፍሎች በተጨማሪም ተከፍለዋል፡፡ አስራሁለቱ ትንንሽ አስተዳደሮች የከተማ ደረጃ ያላቸው ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሉክሰምበርግ ከተማ ትልቋ ነች፡፡
የውጭ ግንኙነት
ሉክሰምበርግ ለረጅም ዘመን የአውሮፓ ፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ውሕደትን በዋነኛነት ስትደግፍ ቆይታለች፡፡ የአውሮፓን ውሕደት በሚተነብየው ጥረታቸው ሉክሰምበርግ እና ቤልጂየም በ1921 እ.ኤ.አ. የቤልጂየም-ሉክሰምበርግ የኢኮኖሚክ ሕብረትን የመሰረቱ ሲሆን ይሄም ልውውጥ የሚደረግበት መገበያያ ገንዘብ ለመፍጠር እና የጋራ እሴት እንዲኖር ያለመ ነበር፡፡ ሉክሰምበርግ የቤኔሉክስ የኢኮኖሚ ሕብረት አባል እና የአውሮፓ ኢኮኖሚ ማሕበረሰብ (አሁን የአውሮፓ ሕብረት) አባል ናት፡፡ በተጨማሪም በሸንጀን ቡድን ውስጥ (ስምምነቱ በተፈረመባት የሉክሰምበርግ መንደር ስም የተሰየመ) የተሳተፈች ሲሆን፣ ግቡም በአባል ሐገራት መካከል የሚደረግ ነፃ ዝውውር ማለት ነው፡፡ በዚሁ ጊዜ አብዛኛው የሉክሰምበርግ ዜጎች የአውሮፓ ሕብረት ስሜት የሚኖረው በፍተኛ የትራንስ አትላንቲክ ግንኙነት ግንዛቤ ውስጥ እና ፕሮ-ናቶ፣ ፕሮ-ዩኤስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን የሚከተል ይሆናል፡፡
ሉክሰምበርግ የአውሮፓውያን የፍትህ ፍርድ ቤት፣ የአውሮፓ አዲተሮች ፍርድ ቤት፣ የአውሮፓ ሕብረተሰብ የስታቲስቲክ ጽ/ቤት (“ዩሮስታት”) እና ሌሎች አስፈላጊ የኢዩ አካላት መቀመጫ ናት፡፡ የአውሮፓ ፓርላማ ሴክሬተሪያት በሉክሰምበርግ የሚገኝ ሲሆን ነገር ግን ፓርላማው በአብዛኛው የሚሰበሰበው በብሩሰልስ እና አልፎ አልፎም በስትራስቡርግ ነው፡፡
ወታደር
ሉክሰምበርግ በመከላከያ ሐይሉ እና በናቶ ውስጥ በጅጉ አነስተኛ የሆነ የጦር ሰራዊት ያላት ሲሆን እስከ 800 የሚጠጉ ወታደሮች እና 100 የመንግስት ሰራተኞች ናቸው፡፡ በየብስ የተከበበች ሐገር እንደመሆኗ የባሕር ሐይል የላትም፡፡
ሉክሰምበርግ በተጨማሪም የአየር ሐይል የሌላት ሲሆን፣ ይሁንና የናቶ 17 ኤደብሊውኤሲኤስ አውሮፕላኖች እንደሁኔታዉ የሉክሰምበርግ አውሮፕላኖች ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ ከቤልጂየም ጋራ ባደረገችው የጣምራ ስምምነት ሁለቱም ሀገራት ለአንድ ኤ400ኤም ወታደራዊ ካርጎ አውሮፕላን የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
መልክዐ ምድር
ሉክሰምበርግ በአውሮፓ አንዷ እጅግ ትንሽ ሐገር ናት እንዲሁም የአለማችን 194 ነጻ ሐገራት በስፋቷ 179ኛ በመሆን ተቀምጣለች፡፡ ሐገሪቱ በስፋቷ 2,586 ስኩዌር ኪሎሜትር (998 ስኩ. ማ) ስትሆን እንዲሁም ርዝመቷ 82 ኪሜ (51 ማይ) እና 57 ኪሜ (35 ማ) ወርድ አላት፡፡ በ490 እና 510 ሰ ላቲቲውድ እና 50 እና 70 ምስ ሎንግቲውድ መካከል ትገኛለች፡፡
በምስራቅ ሉክሰምበርግን የጀርመን የቡንደስላንድ ሪኔላንድ-ፓላቲኔት እና ሳርላንድ ሲያዋስናት እና በስተደቡብ የፈረንሳይዋ ክልል ሎሬይን ታዋስናታለች፡፡ ታላቋ የመስፍን ሐገር የቤልጂየሟ ዋሉን ክልል የምትዋሰን ሲሆን፣ በተለይ ኋላ የተመለከተችው የሉክሰምበርግ ግዛት እና ሊዬጅ፣ ከፊሎቹ ጀርመንኛ ተናጋሪ የቤልጂየም ማሕበረሰብን ያቀፈ ሲሆን፣ በምዕራብ እና በሰሜን በተከታታይ ናቸው፡፡
የሐገሪቱ ሰሜናዌ ሩብ ክፍል “ኦዬስሊንግ” በመባል የሚታወቁ ሲሆን እና የአርዴኔስ ግማሽ ክፍል ናቸው፡፡ ኮረብታማ እና ዝቅተና ተራሮችን የያዘ ሲሆን የክኔይፍ አቅራቢያ ዊልዌርዴጅ፣ ከፍታ ላይ የሚገኘውን ነጥብ፣ በ560 ሜ (1,837 ጫማ) ነው፡፡ ሌሎች ተራሮች “ቡርግፕላዝ” 559 ሜትሮች ሁልዳንጅ አካባቢ እና “ናፖሌዎንስጋርድ” በ 554 ሜትሮች ራምብሮች አካባቢ ናቸው፡፡ ክልሉ በተራራቀ መልኩ ህዝብ የሰፈረበት ሲሆን አራት ሺህ በላይ በሚደርስ ህዝብ ባለበት አንድ ከተማ ብቻ ይገኛል (ዊልትዝ)፡፡
የሐገሪቱ ደቡባዊ ሁለት ሶስተኛ ክፍል “ጉትላንድ” በመባል የሚጠራ ሲሆን ከኦየስሊግ ይልቅ ህዝብ ተጠጋግቶ የሚኖርባት አካባቢ ናት፡፡ በተጫሪም ይበልጥ ብዝሐነር ያላት እና በአምስት የመልክዐምድር ክፍሎች የምትከፈል ናት፡፡ የሉክሰምበርግ አምባ በደቡብ ማዕከላዊ ሉክሰምበርግ ሰፊ፣ ዝርግ፣ አሸዋማ ድንጋ የሚበዛባት ቦታ እንዲሁም የሉክሰምበርግ ከተማ ሳይት ናት፡፡ ከሉክሰምበርግ ምስራቅ አቅጣጫ ትንሷ ስዊትዘርላንድ ኮረብታማ ገፅታ እና ጥቅቅ ያሉ ደኖች ያሉበት ስፍራ ነው፡፡ የሞሴል ሸለቆ ዝቅተኛው ቦታ ሲሆን በደቡባዊው ምስራቅ ድንበር ታኮ የሚሄድ ቦታ ነው፡፡ ሬድ ላንድስ በደቡባዊው ጫፍ እና በደቡባዊው ምዕራብ የሉክሰምበርግ የኢንዱስትሪ ልብ እና የሉክሰምበርግ ትልልቅ ከተሞች መገኛ ቦታ ነው፡፡
የሉክሰምበርግ እና የጀርመን ድንበር ላይ ሶስት ወንዞች ያሉ ሲሆን እነዚህም ሞሴል፣ ሳውየር፣እና ኦውር ናቸው፡፡ ሌሎች አበይት ወንዞች አልዜት፣ ክሌርቭ፣ እና ዊልትዝ ናቸው፡፡ የሳውር መካከል እና አተርት ሸለቆ በጉትላንድ እና ኦዬስሊንግ ድንበር መካከል ነው፡፡
በ2012 እ.ኤ.አ. የአካባቢ ደረጃ መጣኝ መሰረት ሉክሰምበርግ በአካባቢ ጥበቃ ምዘና ከተደረገባቸው 132 ሐገራት መካከል በደረጃ አራተኛዋ የተሻለች ፈጻመሚ ናት፡፡ በሜርሰርስ ከወጡት ለመኖ የሚመቹ ምርጥ 10 ሐገራት መካከል ሉክሰምበርግ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
አየር ንብረት
ሉክሰምበርግ የባሕር አይነት የአየር ንብረት ያላት ሲሆን (ኮፐን፡ ሲኤፍቢ)፣ በተለይ በክረምት መገባደጃ ከፍተኛ ዝናብ ይኖራታል፡፡ ክረምቶች ዋቃት እና በጋዎች ቀዝቃዛ ናቸው፡፡
ትራንስፖርት
ሉክሰምበርግ አመቺ የሆነ የመንገድ፣ የባቡር እና የአየር ትራንስፖር ፋሲሊቲዎች እና አገልግሎቶች አሏት፡፡ የመንገድ ኔትወርክ በቅርብ አመታት በጉልህ ዘመናዊ ሲሆን 147 ኪሜ (91ማይ) የሞተር መንገዶች መዲናዋን ከአጎራባች ሐገራት ጋራ ያገናኟታል፡፡ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ፓሪስ ድረስ የሚያገናኘው የቲጂቪ አገናኝ መምጣት የከተማዋ የባቡር ጣቢያ እንዲታደስ ያደረገ ሲሆን እና በ2008 እ.ኤ.አ. በሉክሰምበርግ አየር ማረፊያ አዲስ የተሳፋሪዎች ተርሚናል ተከፍቷል፡፡ በመዲናዋ የከተማ የኤሌክትሪክ ባቡር እንዲሁም ቀላል ባቡር በአቅራቢያ አካባቢ ዎች በቀጣይ ጥቂት አመታት የማስተዋወቅ እቅድ አለ፡፡
በሉክሰምበርግ በ1000 ሰዎች 680.1 ተሽከርካሪዎች አሉ ይኸውም ከሁለቱ የሞናኮ መስተዳድር እና የብሪቲሽ የውጭ ግዛት ከሆነችው ጂብራልታር በስተቀር ከሁሉም በላይ ነው፡፡
ግንኙነቶች
በሉክሰምበርግ የቴሌኮሙኒኬሽን ኢንዱስትሪ ከፓለቲካ ተፅዕኖ ነጻ ሲሆን እና የኤሌክትሮኒክ ኔትወርኮች በጉልህ ደረጃ አድገዋል፡፡ በተለያዩ ኦፕሬተሮች መካከል ያለው ውድድር በ2011እ.ኤ.አ. በወጣው ፓኩዌት ቴሌኮም የመንግስት የህግ ረቂቅ ማዕቀፍ ዋስትና ተሰጥቷቸዋል ይኸውም የአውሮፓውያንን የቴሌኮም መመሪያዎች ወደሉክሰምበርግ ህግ የተለወጠ ነው፡፡ ይኸውም የኔትወርክ እና አገልግሎቶችን ኢንቨስትመንት ያበረታታል፡፡ ተቆጣጣሪው አይኤልአር- ኢንስቲቱት ሉክሰምቦርጂስደ ሬጉሌሽን ለማሕበራቱ በእነዚህን ደንቦች ተገዢ እንዲሆኑ ማረጋገጫ ያቀርባል፡፡
ስነ-ህዝብ
ዘር
የሉክሰምበርግ ህዝብ ሉክሰምበርጋዊያን በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከቤልጂየም ፣ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ጀርመን እና ፖርቱጋል አብዛኞቹ በኋላ ላይ ከተጠቀሰው መጡ ሆነው በመበራከታቸው የተነሳ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ስደተኛ ህዝብ በቅጥር እድገት አሳይቷል፡፡ በ2013 እ.ኤ.አ. የፖርቱጋል ዜግነት ያላቸው 88,000 ነዋሪዎች ነበሩ፡፡
በተጨማሪም ጥቂት የሚባሉ የሮማኒ (ጂፕሲ) እና የአይሁድ ህዝቦች አሉ፡፡ ሁለቱ በሉክሰምበርግ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ከፍተኛ ጭፍጨፋ ደርሶባቸው ከሉክሰምበርግ እንዲወጡ ሆኗል፡፡
ከዩጎዝላቭ ጦርነት ጅማሬ አንስቶ ሉክሰምበርግ ከቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና፣ ሞንቴኔግሮ፣ እና ሰርቢያ በርካታ ስደተኞችን አስተናግዳለች፡፡ በአመት ከ10,000 በላይ አዳዲስ ስደተኞች ወደሉክሰምበርግ ይደርሳሉ፣ አብዛኞቹም ከአሕ ሐገራ ናቸው እንዲሁም አምስራቅ አውሮፓ ናቸው፡፡ በ2000 እ.ኤ.አ. በሉክሰምበርግ 162,000 ስደተኞች በሉክሰምበርግ ነበሩ እነዚህም የህዝብ ቁጥሩን 37 በመቶ ይሆናሉ፡፡ በሉክሰምበርግ በግምት 5,000 ህገወጥ ስደተኞች በ1999 ነበሩ፡፡
ቋንቋ
በሉክሰምበርግ ሶስት ቋንቋዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡ እነዚህም ፈረንሳይኛ፣ ጀርመን፣ እ ሉክሰምበርጊሽ ሲሆኑ የሞስሌ ክልል ፍራንኮኒያን ቋንቋ በቤልጂየም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን አጎራባች ክፍሎች ይነገራል፡፡ ምንም እንኳን ሉክሰምበርጊሽ የጀርመን ምዕራብ ማዕከላዊ ከፍተኛ የጀርመን ቋንቋዎች ቡድን ቢሆንም ከ5000 በላይ የሆኑ የቋንቋው ቃላት መሰረታቸው ከፈረንሳይኛ ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ የታተሙ የሉክሰምበርጊሽ አረፍተ ነገሮች በሳምንታዊው “ሉክሰምበርገር ዎቼንብላት” ጋዜጣ ሁለተኛው እትም በአፕሪል 14 1821 እ.ኤ.አ. ላይ ይታሉ፡፡
ከሶስቱ አንዱ ይፋዊ ቋንቋ እንደመሆኑ ሉክሰምበርጊሽ የከፍተኛው መስፍን ብሔራዊ ቋንቋ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
እያንዳንዳቸው ሶስቱ እንደዋነኛ ቋንቋ በመሆን በተወሰኑ ሁኔታዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የሉክሰምበርግ የትምህርት ስርአት በሶስት ቋንቋ የተዘጋጀ ነው፡ የመጀመሪያዎቹ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት አመታት በሉክሰምበርጊሽ ሲሆኑ፣ ወደጀርመን የሚቀየር ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ የመማር ማስተማሩ ቋንቋ ወደፈረንሳይኛ ይለወጣል፡፡ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ በሶስቱ ቋንቋዎች ብቁ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል፡፡
በትምህርት ቤት እንግሊዝኛ ትምህርት የሚሰጥ በመሆኑ በተለይ በሉክሰምበርግ ሲቲ ሰዎች እንግሊዝኛ መናገር ይችላሉ፡፡ ፈረንሳይኛ የመንግስት ተመራጭ ቋንቋ ነው፡፡
ሐይማኖት
ሉክሰምበርግ ሐይማኖትን የማትቀበል ሐገር ናት ሆኖም ሐገሪቱ የተወሰኑ ሐይማኖቶችን በይፋ ሁሉም ሊከሉት የሚገባ ሐይማኖት በማድረግ እውቅና ይሰጣል፡፡ ይሄ ሐገሪቱ በሐይማኖት ላይ የማስተዳደር እና ካሕናትን በመምረጡ ረገድ ሚና እንዲኖራት ያስችላል፣ ለዚህም በተለዋጭ የተወሰኑ የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን እና ምንዳ ይከፍላል፡፡
ከ1980 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግስት በሐይማኖታዊ እምነቶች ወይም ልማዶች ላይ ስታቲስቲክስ መሰብሰቡ ህገወጥ ነገር ሆኖ ቆይቷል፡፡ በሲአይኤ ፋክትቡክ ግምት መሰረት በ2000 እ.ኤ.አ. ዓመት 87% ሉክሰምበርጎች የንጉሳዊያን ቤተሰቦችን ጨምሮ ካቶሊኮች ሲሆ፣ ቀሪዎቹ 13% ሙስሊሞች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች፣ እና ሐይማኖት የለሾች ናቸው፡፡ በ2010 ፒው የምርምር ማዕከል ጥናት መሰረት 70.4% ክርስቲያኖች፣ 2.3% ሙስሊሞች፣ 26.8% ምንም ዝንባሌ የሌላቸው፣እና 0.5% ሌሎች ሐይማኖቶች ናቸው፡፡
የሉክሰምበርግ 2012 የሐይማኖት ዝንባሌዎች
የሮማ ካቶሊክ (67%) ፕሮቴስታንት (3%) ኦርቶዶክስ ክርስቲያን (1%) ሌሎች ክርስቲያኖች (3%) ሙስሊም (3%) ቡድሐዎች (1%) ሌሎች ሐይማኖቶች/አግኖስቲክ (14%) በእግዚአብሔር የማያምኑ (6%) ያልታወቁ (1%) |
ትምህርት
የሉክሰምበርግ ዩንቨርሲቲ እና የሉክሰምበርግ ሚያሚ ዩንቨርሲቲ ግቢዎች ሉክሰምበርግ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ዩንቨርሲቲዎች ናቸው፡፡
ጤና
ሉክሰምበርግ በአውሮፓ ውስጥ በነፍስ ወከገፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን አልኮል ትሸጣለች፡፡ ይሁንና ከአጎራባች ሐገራት ደንበኞች የሚገዛው ከፍተኛ ቁጥር ያለው አልኮል በስታቲስቲክስ በነፍስወከፍ ከፍተኛ የአልኮል ሽያጭ ሲሆን ይሄ የአልኮል ሽያጭ ደረጃ የሉክሰምበርግ ህዝብን ትክክለኛ የአልኮል ሽያጭ አይወክልም፡፡
ባሕል
ሉክሰምበርግ በጎረቤቶቿ ባሕል ተሸፍና ቆይታለች፡፡ በርካታ ባሕሎች አሏት በርካታዉ ሕብረተሰብ በገጠራማው ክፍል የሚኖር ነው፡፡ በአብዛኛው በመዲናዋ የሚገኙ በርካታ ታዋቂ ሙዚየሞች አሏት፡፡ እነዚህም የታሪክ እና ስነ-ጥበብ ብሄራዊ ሙዚየም፣ የሉክሰምበርግ ከተማ ታሪክ ሙዚየም፣ እና አዲሱ ከፍተኛው መስፍን ጂን የዘመናዊ የስነ-ጥበብ ሙዚየም (ሙዳም) ናቸው፡፡ በዲየኪርች የሚገኘው የብሔራዊ ወታደራዊ ታሪክ ሙዚየም የቡልጅ ታሪክን በመወከሉ በልዩ ሁኔታ ይታወቃል፡፡ የሉክሰምበርግ ከተማ ራሷ በምሽጎቿ ታሪካዊ አስፈላጊነት ረገድ በዩኔስኮ የአልም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ገብታለች፡፡
ሐገሪቱ የተወሰኑ በአለማቀፍ ደረጃ የታወቁ ከያኔያን ያሏት ሲሆን እነዚህም ሰዐሊው ቴዎ ኬርግ፣ ጆሴፍ ኩተር እና ሚሼል ማጄሩስ እና በዩኔስኮው የአለም መዝገብ ትውስታ ላይ የሰው ዝርያ በሚል የተቀመጠለት የፎቶግራፍ ባለሞያው ኤድዋርድ ስቴይቼን እና አሁን በክሌርቫውክስ በቋሚነት የሚገኘው ነው፡፡ የፊልም ኮከብ የሆኑት ሎሬታ ያንግ የሉክሰምበርጊሽ ዝርያ ያላቸው ግለሰብ ናቸው፡፡
ሁለት ጊዜ የአውሮፓ የባሕል መዲና በመባል የተሰየመች ጀየመጀመሪያዋ ከተማ ናት፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1995 እ.ኤ.አ. ነው፡፡ በ2007 የአውሮፓ የባህል መዲና የሉክሰምበርግን ከፍተኛ መስፍን ሬይንላንድ-ፕፋልዝ እና በጀርመን የምትገኘውን ሳርላንድ፣ የዋሉን ክልልን እና ጀርመንኛ ተናጋሪ የሆነውን የቤልጂየም ክፍል እና በፈረንሳይ የሚገኘውን ሎሬን ክልል አካታ ድንበር ተሻጋሪ ሆናለች፡፡
ስፖርት
በአውሮፓ ካሉት በርካታ ሐገራት በተለየ መልኩ የሉክሰምበርግ ስፖርት በአንድ ብሔራዊ ስፖርት ላይ የተወሰነ አይደለም ነገር ግን ቡድን እና በግል በርካታ ስፒርቶችን ያካትታል፡፡ ከ521,353 ሕዝቧ 10,000 የአንደኛው ወይም የሌላኛው ስፖርት ፌዴሬሽን ፈቃድ ለው አባ ነው፡፡ ትልቁ የሐገሪቱ የስፖርት ማዕከል ድኮክ የሚሰኘው በሉክሰምበርግ ሰሜናዊ ምስራቅ አቅጣጫ በኪርችበርግ የሚገኘው የቤት ውስጥ ሜዳ እና የኦሎምፒክ መዋኛ ገንዳ ሲሆን 8300 ሰዎችን መያዝ ይችላል፡፡ ሜዳው ለቅርጫት ኳስ፣ ለእጅ ኳስ፣ ጂምናስቲክ፣ እና የመረብ ኳስ ሜዳዎችን የሚያካትት ነሲሆን የ2007 እ.ኤ.አ. የአውሮፓ የሴቶች መረን ኳስ የፍጻሜ ጨዋታን ጨምሮ አ ስተናግዷል፡፡
ታዋቂ የስፖርቱ ሰዎች፡
· አልፓይን ስኪየር ማርክ ጊራርዴሊ ከ1985 እና 1993 እ.ኤ.አ. መካከል ለአምስት ጊዜ የአለም ዋንቻ አጠቃላይ ሻምፒዮና
· ሳይክሊስት ኒኮላስ ፍራንትዝ፣ የ1927 እና 1928 እ.ኤ.አ. ቱር ደ ፍራንስ አሸናፊ፣ ቻርሊ ጋውል የ1956 እና 1959 እ.ኤ.አ. ጊሮ ደኢታሊያን እና በ1959 እ.ኤ.አ. የቱር ደ ፍራንስ አሸናፊ፣ ኤልሲ ጃኮብስ፣ በ1958 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያዋ የሴት የመንገድ የአለም ሻምፒዮን፣ እና አንዲ ሽሌክ የ2010 ቱር ደ ፍራንስ አሸናፊ፡፡
· የመካከለኛ ርቀት ሯጭ ጆሲ ባርቴል፣ በ1952 እ.ኤ.አ. የክረምት ኦሎምፒክ የወንዶች 1500 ሜትር አሸናፊ፡፡
· 1961 እ.ኤ.አ. የአለም የውሐ ስኪ ሻምፒዮን ሳይልቪ ሁልሴማን
· የቴኒስ ተጫዋች ጊልስ ሙለር፣ አን ክሬመር እና ማንዲ ሚኔላ
ምግብ
የሉክሰምበርግ ምግብ በላቲን እና በጀርመን አለማት መካከል ያለውን ድንበር የሚያንጸባርቅ ሲሆን በአጎራባች ፈረንሳይ እና ጀርመን ምግቦች በከፍተኛ ሁኔታ ተፅዕኖ አድሮበታል፡፡
መገናኛ
የሉክሰምበርግ ሚዲያ አበይት ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ እና ጀርመንኛ ነቸው፡፡ ሰፊ ስርጭት ያለው ጋዜጣ በጀርመን ቋንቋ የሚወጣው የዕለት ሉክሰምበርግ ወርት ነው፡፡ ፖርቱጊውዝ እና እንግሊዝኛ የራዲዮ እና ብሔራዊ የህትመት ሚዲያዎች አሉ፡፡
ሉክሰምበርግ በራዲዮ እና በቴሌቪዥን ጣቢያዎቿ በመላው አውሮፓ ትታወቃለች፡፡ ሉክሰምበርግ በሚስተር ሁብሎት አማካኝነት አኒሜትድ ፊልም ዘውግ በ2014 እ.ኤ.አ. የኦስካር አሸናፊ ሆናለች፡፡
በተጨማሪም የሚከተሉትን ይመልከቱ
· የሉክሰምበርግ ማውጫ
· የሉክሰምበርግ አርክቴክቸር
· በሉክሰምበርግ የንጉሳውያን መኖሪያዎች ዝርዝር
· የሉክሰምበርግ ሐይቆች
· የውጭ ዕዳ ያለባቸው ሐገራ ዝርዝር
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.