From Wikipedia, the free encyclopedia
Þ, þ (þorn /ሶርን/) በአይስላንድኛ፣ በጥንታዊ እንግሊዝኛ እና በጥንታዊ ኖርስኛ የተገኘ ፊደል ነው።
በዘመናዊ እንግሊዝኛ እንዲሁም በዘመናዊ ስካንድናቪያ ልሳናት (ኖርዌኛ፣ ስዊድኛ፣ ዳንኛ)፤ የዚሁ ፊደል ድምጽ በሁለት ፊደላት በ«TH» በመወከሉ፣ የፊደሉ «Þ» ጥቅም ተተክቷል። «Þ» ዛሬ የሚታየው በአይስላንድኛ ጽሕፈት ብቻ ነው።
አጠራሩ በአማርኛ የማይሰማ ድምጽ ነው። ይህ ድምጽ ምላሱን ከላይኛው ጥርሶች በታች በመዘርጋት የሚፈጠር ነው። የውጭ ቋንቋ አጠራር በአቡጊዳ ጽሕፈት ለመግለጽ፣ ብዙ ጊዜ ይህ ድምጽ በ«ሰ» ወይም በ«ዘ» (ከነመስመሩ) ይወከላል።
ጥንታዊ እንግሊዝኛ አስቀድሞ ፉሶርክ በተባለው ሩን ጽሕፈት ይጻፍ ነበር። ክርስትና በእንግሊዝ አገር ከተቀበለ በኋላ ግን፣ ቋንቋው በላቲን አልፋቤት ሊጻፍ ጀመረ። ይህ ድምጽ በሮማይስጥ ሰለማይታወቅ፣ በላቲን አልፋቤትም ለዚሁ ድምጽ ምንም ፊደል ባለመኖሩ፣ የ«Þ» ቅርጽ የተወሰደው ከፉሶርክ ጽሕፈት ከፊደሉ ነበር። ስሙም «ሶርን» (እሾህ) ከዚህ ሩን ስም ተወሰደ። በጥንታዊ ኖርስና አይስላንድኛ ደግሞ እንደዚያ ነበር፣ ነገር ግን የሩን ፊደል ስም «ሱርስ» (ረጃጅም) ይባል ነበር።
በነዚህ ልሳናት፣ አንድ ሌላ ፊደል «Ð, ð» ከ«Þ» ጋር የሚለዋወጥ ነበር። ሁለት የተለያዩ ድምጾች («ሰ» እና «ዘ») ቢወክሉም፣ ፊደሎቹ ግን አልተለያዩም። በዘመናዊ አይስላንድኛ ግን Þ ለ ሰ፤ Ð ለ ዘ ይወሰናል።
በእንግሊዝኛ ከ1300 ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ፣ ድምጹ በሁለት ፊደላት (TH) መጻፍ ቄንጡ ሆነ። የ«Þ» ጥቅም እንግዲህ በየጥቂቱ ጠፋ። ሆኖም የእንግሊዝኛ ቃል «the» (መስተጻምሩ) ለረጅም ጊዜ «Þe» በመጻፉ ቆየ። በጊዜ ላይ፣ የዚህ አጻጻፉ እንደ «ye» ይመስል ጀመር። እስከ ዛሬም ድረስ፣ አንዳንድ ባለ ሱቅ ወይም ቡና ቤት የድሮ ባህል ሁኔታ ለማምሰል፣ በስማቸው ላይ «Ye Olde» («ጥንታዊው») ሲጨምሩ ከዚህ ልማድ የተነሣ ነው (ምሳሌ፦ «Ye Olde Pizza Parlor»፣ ወይም «ጥንታዊው ፒጻ ቤት»)። አብዛኞቹ ደንበኞች ግን የፊደሉን ታሪክ ባለማውቃቸው፣ አጠራሩ /ዪ ኦልድ/ እንደ ሆነ በማለት ይስታሉ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.