አማርኛ From Wikipedia, the free encyclopedia
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ
አልፍ (ወይም አሌፍ) በአቡጊዳ ተራ መጀመርያው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች መጀመርያው ፊደል አሌፍ ይባላል። በዓረብኛ ፊደል ደግሞ መጀመርያው ፊደል አሊፍ ሲሆን በግሪክም አልፋ ይባላል።
በመጀመርያ በግዕዝ የዚህ ምልክት ምክንያት ተፈናጣሪ ተናባቢ ድምጽ ለማመልከት ነበር። ይህ ድምጽ ፍች «ነዛሪ የጉሮሮ እግድ» ይባላል።[1] በዛሬው አማርኛ ግን ምንም ተናባቢ ሳይኖር አናባቢ ብቻ ሊያመለከት ይችላል። (በዘመናዊ ዕብራይስጥም «አሌፍ» እንዲህ ይጠቅማል።) በዚህ ጥቅም በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከዐይን (ዐ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል።
በአረብኛ ደግሞ «አሊፍ» ከጥንት ተፈናጣሪ ተናባቢ ድምጽ ነበር። በኋላ ግን 'አ' የሚለውን አናባቢ ብቻ ሊያመልከት መጣ። ስለዚህ ነዛሪ የጉሮሮ እግድ ለመጻፍ ሌላ አዲስ ፊደል «ኅምዛ» ተፈጠረ።
በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (አ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ«ኸ» አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ኣ) አንድላይ ነው። ቢሆንም አንዳንዴ በባዕድ ቃላት ይህ አናባቢ በቃል መጀመርያ ሲጋጠም «ኧ» የሚለው ልዩ ፊደል አለ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.