From Wikipedia, the free encyclopedia
ጀድኸፐረው ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ለአጭር ጊዜ በ1781 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የሰኸምሬኹታዊ ኻውባው ተከታይ ነበረ።
==
ጀድኸፐረው | |
---|---|
ይህ «የኦሲሪስ አልጋ» የተባለው ቅርስ በጀድኸፐረው ዘመን በጥንታዊ ፈርዖን ጀድ መቃብር ገባ። | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1781 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው |
ተከታይ | ሰጀፋካሬ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | ሆር አዊብሬ? |
==
ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ የለም። ሆኖም ከሥነ ቅርስ ረገድ ፈርዖንነቱ እርግጥኛ ነው። ስሙ ከቶሪኖ ዝርዝር ጠፍቶ የኻውባው ተከታይና ወንድም እንደ ነበር ይታስባል፤ በ«ኦሲሪስ አልጋ» በተባለው ቅርስ ላይ ሌላ ስሙ (የአባት ስም) «ሆር» (ሆር አዊብሬ) እንደ ነበር ይመስላል። በተጨማሪ የጀድኸፐረው ስም በ፲፩ ማኅቴሞች ላይ በአባይ ፪ኛው ሙላት አካባቢ (በኩሽ መንግሥት ጠረፍ) ሲገኝ ማኅተሞቹ ከቀዳሚው ከኻውባውና ከታችኛው ግብጽ ፈርዖን ከሸሺ ማዓይብሬ ማኅተሞች አጠገብ ተገኙ።
የጀድኸፐረው ተከታይ ሰጀፋካሬ (ካይ-አመነምሃት) ምናልባት ልጁ ነበር።
ቀዳሚው ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ሰጀፋካሬ |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.