From Wikipedia, the free encyclopedia
የእጅ መድፍ ከሁሉ ጠብመንጃ አይነቶች አስቀድሞ የተፈጠረው ሲሆን የጠመንጃና የመድፎች ሁሉ አባት ሊባል ይችላል።
መጀመርያው የእጅ መድፍ የተሠራው 1120 ዓ.ም. አካባቢ በቻይና አገር ነበር። ባሩድ በቻይና ተገኝቶ ጥቅሙ እንደ የጦርነት መሣርያ በ1036 ዓም ዉጂንግ ዞንግያው በተባለ ጽሑፍ ተጻፈ። ከዚህም በፊት የእሳት ፍላጻ ከ896 ዓ.ም. ጀምሮ፣ የነበልባል ጦር ከ950 ዓ.ም. ግድም ባሩድን ይጠቅሙ ነበር። «የነበልባል ጦር» እንደ ተራ ጦር ሳይሆን ጥቂት ጠጠሮች በባሩድ ተተኩሰው ጭምር ያቀረበ መሣርያ ነበር።
በ1120 ዓ.ም. የተሳለ በስርቿን የተገኘ የዋሻ ስዕል መጀመርያ የእጅ መድፍ ያሳያል። ለጊዜው ይህ ቴክኒክ የቻይናውያን ምስጢር ብቻ ሆኖ ቆየ። ከ1211 ዓም ጀምሮ ግን ሞንጎሎች በመድፍ እርዳታ ግዛታቸውን ያስፋፉ ጀመር። ሞንጎሎችም በ1233 ዓም በሞሂ ውግያ በሀንጋሪ መድፎች በአውሮጳውያን ሠራዊት ላይ መጀመርያ ተኮሱ። ዓረቦች ከዚያ ቀጥሎ ምስጢሩን እንዳገኙ ይመስላል፤ በ1252 ዓ.ም በአይን ጃሉት ውግያ በዛሬው እስራኤል፣ ማምሉኮች ከግብጽ በሞንጎሎች ላይ መድፎች እንደ ነበሩዋቸው፤ እንዲሁም በእስፓንያ የካስቲል ንጉሥ 10ኛው አልፎንሶ በ1254 ዓም ኒዬብላን ከተማ በሠራዊት ሲከብብ፣ ዓረቦቹ በመድፍ ተከላከሉዋቸው።
መጀመርያዎቹ እጅ መድፎች የተሠሩ ከቀርቀሃ ሲሆን ከ1280 ዓ.ም. ያህል ጀምሮ ከነሓስ ሊሠሩ ጀመር። ባሩድ በበርሚል ገብቶ ድንጋይ ሲጨመር ከዚያም እሳት ሲነካው በበርሚል አቅጣጫ ይፈነዳል። በቅርብ ጊዜ ውስጥ መድፍ በሕንድም ሆነ በጣልያን ይሠራ ጀመር፤ በ1300ዎቹ ውስጥ በመላው አውሮጳና እስያ ተስፋፋ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.