From Wikipedia, the free encyclopedia
ነሐሴ ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፪ ቀናት ይቀራሉ።
ከኢትዮጵያን ሪፖርተር ፦ "ሆያ ሆዬ" በሚል አርስት ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም የወጣ አንቀጽ
"መጣና ባመቱ አረ እንደምን ሰነበቱ ክፈትልኝ በሩን የጌታዬን ሆያ-ሆዬ-ሆ"
እያሉ ልጆች በዜማ እያወረዱ፣ በየመንደሩ እየተሽከረከሩ የሚጫወቱት ለቡሄ በዓላቸው ነው፡፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ፣ አሁንም እየቀጠለ ያለ ትውፊት ነው፡፡
ዛሬ ነሐሴ ፲፫ ቀን የበዓሉ ክብር ነው፡፡ በተለይ ነባሩን ትውፊት ይዞ የሚገኘው በገጠር አካባቢ ነው፡፡ ቡሄኞቹ ልጆች ለበዓሉ አስቀድመው ይዘጋጃሉ፡፡ ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለበዓሉ የሚሆን ሙልሙል ዳቦ ያዘጋጃሉ፡፡ እየጨፈሩ ለሚመጡ ልጆችም ያበረክታሉ፡፡
በአዲስ አበባ ባሁን ጊዜ እየዞሩ ከሚጨፍሩት ሕፃናት ሌላ በከተማዋ ዳርቻ የሚኖሩ ጎረምሶችም በኦሮምኛ የቡሄ ጭፈራቸውን፣ ቄጠማ እያበረከቱ የሚያስኬዱበት ሥርዓት አላቸው፡፡
ቡሄ ጎላጣ፣ መላጣ ማለት እንደሆነ መጻሕፍት ይገልጻሉ፡፡ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ የሚታይበት እንደሆነ ይታመንበታል፡፡
ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት ስለማይኖርም "ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፣ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት" እየተባለም ይነገራል፡፡
ለባህላዊው በዓል መሠረት የሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ጊዜ በታቦር ተራራ ላይ (ደብረ ታቦር) ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት ዕለት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.