X
From Wikipedia, the free encyclopedia
X / x በላቲን አልፋቤት ሀያ አራተኛው ፊደል ነው።
More information ግብፅኛ ጀድ, ቅድመ ሴማዊ (አልተገኘም) ...
Close
More information የላቲን አልፋቤት, ተጨማሪ ምልክቶች፦ ...
Close
የ«X» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ቢታስብም እስካሁን አልተገኘም። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አንዳንድ ሊቃውንት የ"ዓምድ" ("ጀድ") ስዕል እንደ ነበር ይገምታል።
ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ለድምጹም /ስ/ አገለገለ።
በግሪክኛ ግን ከ«ሺን» የደረሰው «ሲግማ» ለ/ስ/ ስላገለገለ፣ ከሳሜክ የደረሰው ቅርጽ «Ξ» በምስራቃዊ ግሪክ አልፋቤት ለድምጹ /ክስ/ ይወከል ጀመር። ሌላ አዲስ ቅርጽ «Χ» በምሥራቅ ግሪክ አልፋቤት ለ/ኽ/ ወከለ፤ በምዕራባዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ቅርጽ ለ/ክስ/ ተጠቀመ።
በኤትሩስክኛ አልፋቤት እንዲሁም በላቲን አልፋቤት የ«X» ቅርጽ እንደ /ክስ/ ሆኖ ቆየ። በእንግሊዝኛም ደግሞ አብዛኛው ጊዜ /ክስ/ ያመልክታል። በአንዳንድ ሌሎች ቋንቋዎች ግን ልዩ ልዩ ድምጾች ሊወክል ይችላል።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ሰ» («ሳት») የሚለው ፊደል ከሴማዊው «ሳሜክ» ስለ መጣ፣ የላቲን 'X' ዘመድ ሊባል ይችላል።