4 ሰኑስረት
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰነፈሪብሬ 4 ሰኑስረት በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1592 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
==
Quick Facts ግዛት, ቀዳሚ ...
ሰኑስረት 4 ሰነፈሪብሬ | |
---|---|
የሰኑስረት ሰነፈሪብሬ ሐውልት | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1592 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ ? |
ተከታይ | 2 ደዱሞስ |
ሥርወ-መንግሥት | 16ኛው ሥርወ መንግሥት |
Close
==
ስሙ የሚታወቅ ከአንድ ትልቅ ሐውልት፣ በ1ኛው ዓመት ከተቀረጸ ጽላትና ከአንዳንድ ጥቃቅን ቅርሶች ነው። ከዚህ በላይ በካርናክ ዝርዝር ላይ «ሰነፈር<...>ሬ» የተባለ ፈርዖን ይገኛል።
በቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ ከሰኸምሬ ሸድዋሰት ቀጥሎ አምስት የፈርዖን ስሞች ጠፍተዋል። በአቶ ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ ሰነፈሪብሬ በነዚህ አምስት መካከል ነበሩ።
ቀዳሚው መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1592 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 2 ደዱሞስ |