የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን
From Wikipedia, the free encyclopedia
የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን (አፍሪካንስ፡ Suid-Afrikaanse nasionale sokker span ስዊድ-አፍሪካንስ ናሲዮናል ሶከር ስፓን) ወይም ባፋና ባፋና ደቡብ አፍሪካን ወክሎ በእግር ኳስ ይወዳደራል። አስተዳዳሪው አካል የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ሲሆን መቀመጫው ሶከር ሲቲ ነው። በአሁኑ ጊዜ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፒትሶ ሞሲማኔ ሲሆን አምበሉ ደግሞ ስቲቨን ፒየናር ነው። በደቡብ አፍሪካ በነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ምክንያት ከ1992 እ.ኤ.አ. በፊት ቡድኑ በፊፋ ማዕቀብ ተጥሎበት ነበር። በ2010 እ.ኤ.አ. ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ አገር ስትሆን፣ የቡድኑ ሲፊዌ ሻባላላ የውድድሩን የመጀመሪያ ግብ አግብቷል። የቡድኑ ትልቅ ድል በ1996 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫን ማግኘቱ ነው።