From Wikipedia, the free encyclopedia
አማር-ሲን ከ1918 እስከ 1909 ዓክልበ. ግድም ድረስ የኡርና የሱመር ንጉሥ ነበር። የአባቱ የሹልጊ ተከታይ ነበር። ቀድሞ ስሙ እንደ ቡር-ሲን በሊቃውንቱ ይታነብ ነበር፤ አሁን ግን አጠራሩ «አማር-ሲን» ትክክል እንደ ሆነ ይታመናል።
ለ፱ኝ ዓመቶቹ ሁላቸው በስም ይታወቃሉ። ዘመቻዎች በኡርቢሉምና በተለያዩ ቦታዎች (ሻሽሩም፣ ሹሩድሁም፣ ቢቱም-ራቢዩም፣ ጃብሩና ሑሕኑሪ) ላይ ይመዘገባሉ።[1] በተረፈ አማር-ሲን በኤላማዊ ነገሥታት እንደ ማርሐሺ ንጉሥ አርዊሉክፒ እንደ ዘመተ ይታወቃል። የዑር መንግሥት በአማር-ሲን ዘመን እስከ ስሜናዊ ግዛቶች እስከ ሉሉቢና ሐማዚ ድረስ ተዘረጋ። ደግሞ ዓመጽ በአሹር አሸንፎ አካዳዊ ሻካናካ (ከንቲባ) ዛሪቁም በአሦር ላይ ሾመ።[2]
አማር-ሲን የሱመር ጥንታዊ ሥፍራዎች በተለይ በኤሪዱ የነበረውን ግንብ ለማሳደስ ሠራ።[3]
የባቢሎናዊ «ዋይድነር ዜና መዋዕል የተባለው ሰነድ እንዲህ ይላል፦ «የሹልጊ ልጅ አማር-ሲን የአኪቱ በዓል በሬና በጎች መሥዋዕት ቀየረ። በበሬ ውግያ እንዲሞት ተነበየ፤ ሆኖም ከጫማው መንከስ [ጊንጥ?] ሞተ።»
የአማር-ሲን ልጅ (ወይም ወንድም?) ሹ-ሲን በዑር ዙፋን ተከተለው።
ቀዳሚው ሹልጊ |
የሱመር ነጉሥ 1918-1909 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሹ-ሲን |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.