ነብካውሬ ቀቲ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ነብካውሬ ቀቲ በመጀመርያው ጨለማ ዘመን (9ኛው ወይም 10ኛው ሥርወ መንግሥት) በግብጽ (ከሄራክሌውፖሊስ) የገዛ ፈርዖን ነበረ።
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/5/53/Nebkaure_Khety_Petrie.png)
የነብካውሬ ኅልውና ከሁለት ምንጮች ብቻ ይታወቃል። አንዱ ቅርስ ስሙ የተቀረጸበት የሚዛን ክብደት ሲሆን ሌላው ደግሞ «ልዝቡ ገበሬ» በተባለው ሥነ ጽሑፍ ስሙ ሲጠቀስ ነው።[1] ማዕረጉ «የላይኛና ታችኛ ግብጽ ንጉሥ» ሲሆን መቼ እንደ ገዛ ግን በትክክል አይታወቅም። በአንዳንድ መምህር አስተሳሠብ ይህ ነብካውሬ ቀቲ የመሪካሬ ትምህርት ደራሲ ሊሆን ይችላል፣ ማስረጃ ግን የለም።
- ስለ ነብካውሬ ቀቲ (እንግሊዝኛ)
ቀዳሚው ? |
የግብፅ ፈርዖን 2200-2167 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሰነን-...? |