መኪና መድሃኔ አለም
From Wikipedia, the free encyclopedia
መኪና መድሃኔ አለም በሰሜን ወሎ፣ አቡነ ዮሴፍ ተራራ ውስጥ ከሚገኙ አራት አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ነው። የቤተክርስቲያኑ ህንጻ እንደ ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዋሻ ውስጥ የተስራ ሲሆን አወቃቀሩም ከድንጋይና እንጨት ርብርብ ነው።
Quick Facts ከአለት የተፈለፈለ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን, መኪና መድሃኔ አለም ...
| ||||
---|---|---|---|---|
መኪና መድሃኔ አለም | ||||
መኪና መድሃኔ አለም | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ሌላ ስም | እመኪና መድሃኔ አለም | |||
ዓይነት | ዋሻ ውስጥ ያለ | |||
አካባቢ** | አቡነት ዮሴፍ ተራራ | |||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን | 13ኛው ክፍለዘመን | |||
አደጋ | -- | |||
* የአለበት ቦታ ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |
Close
ከትውፊት አንጻር በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ሲታመን እውስጡ የሚገኙት ጥንታዊ ስዕሎች ግን፣ ልክ እንደ ገነተ ማርያም ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ይመነጫሉ። ስለሆነም፣ ሁለቱንም ቤተክርስቲያኖች አጼ ይኩኖ አምላክ እንዳሰራቸው አሁን ይታመናል[1]።