መትራሃ
From Wikipedia, the free encyclopedia
መትራሃ ደሴት በስሜን ምስራቅ ጣና ሐይቅ 1.5 ኪሎ ሜትር ገባ ብላ የምትገኝ ደሴት ናት። ደሴቲቱ ላይ ብዙ የፈረሱ አብያተ ከርስቲያናት ሲገኙ፣ ከሁሉ ጥንታዊው ቤተክርስቲያን በቀዳማዊ ዳዊት የተሰራ ቢሆንም በግራኝ አህመድ ተቃጥሏል። ኋላ ከተሰሩት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ በቀዳማዊ ዮሃንስ የተሰራው ትልቅ የግምብ ቤተክርስቲያንና የቀዳማዊ እያሱ ቤተ መዘክር ይገኙበታል። ሆኖም እኒህም በደርቡሾች፣ በ1879ዓ.ም. ተቃጥለዋል [1]።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |