From Wikipedia, the free encyclopedia
ፖለቲካ የሚለው ቃል ከግሪኩ ' («ዜጋ») ከሚለው ቃል የመጣ ነው። በአሁኑ ወቅት ፖለቲካ ማለት በቡድን ያሉ ግለሰቦች የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ፖለቲካ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሃገርና ከመንግስት ጋር የተገናኘ ቢሆንም በሌላ አንጻር የሰው ልጆች በቡድን ሆነው በሚገኙበት ማናቸውም ስብስብ ይገኛል፣ ለምሳሌ በኩባንያወች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማኖት መዋቅሮች፣ በቤተሰቦች ውስጥ ሳይቀር ፖለቲካ አለ። የኃይል አመዳደብ፣ የቁጥጥር፣ የውሳኔ ላይ መድረስ፣ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄወች በሁለትና ከዚያ በላይ ባሉ ሰወች መካከል ሲነሱ ያንን ጥያቄ ለመፍታት በሚደረግ ሂደት፣ በዚያ ፖለቲካ አለ። ከዚህ አንጻር በአንዳንዶች አስተሳሰብ አብዮት፣ ጦርነት፣ ማህበረሳባዊ ግጭት ፖለቲካ ሳይሆኑ የፖለቲካ ሂደቱ ክሽፈት ናቸው። በሌሎች አስተያየት እኒህም የአጠቃላይ ሂደቱ አካል ስለሆኑ እንደ ፖለቲካ ይወሰዳሉ።
ፖለቲካን የሚያጠናው የትምህርት አይነት የፖለቲካ ሳይንስ ወይም የፖለቲካ ጥናት ይባላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.