![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/d/d2/Cherokee_Syllabary.svg/langam-640px-Cherokee_Syllabary.svg.png&w=640&q=50)
ጻላጊኛ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጻላጊኛ (ᏣᎳᎩ ᎦᏬᏂᎯᏍᏗ /ጻላጊ ጋዎኒሂስዲ/) በጻላጊ ብሔር የሚነገር በተለይ በአሜሪካ ኖርዝ ካሮላይና እና ኦክላሆማ ክፍላገራት የሚሰማ ቋንቋ ነው። የኢሮኳዊ ቋንቋዎች ቤትሠብ አባል ነው።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/d/d2/Cherokee_Syllabary.svg/640px-Cherokee_Syllabary.svg.png)
በራሱ ጻላጊኛ ፊደል ይጻፋል። ይህ ፊደል ሰኰያ በተባለ የጻላጊ ሊቅ በ1817 ዓም. ግድም ተፈጠረ።
በጻላጊኛ የምላስ ውልብልቢት በታችኛ ጥርስ ግርጌ ይቀመጣል እንጂ እንደ አማርኛ በላይኛ ጥርስ አይደለም።
«ትላ፣ ትሌ፣ ትሊ፣ ትሎ፣ ትሉ፣ ትለን» የሚሉ ፊደላት ደግሞ እንደ «ህላ፣ ህሌ...»፣ «ቅላ፣ ቅሌ...»፣ «ጥላ፣ ጥሌ» ወዘተ. ያሰማሉ።
«ጻ፣ ጼ...» ወዘተ. ደግሞ እንደ «ጃ፣ ጄ...»፣ «ቻ፣ ቼ...» ያሰማሉ። ምሳሌ፦ ᏣᎳᎩ /ጻላጊ/፣ /ጃላጊ/፣ /ቻላጊ/...።
«ህ»፣ «ዕ»፣ «እ» የሚሉ ድምጾች ብዙ ጊዜ በጽሕፈት ባይጻፉም በአጠራር በሰፊ ይጨመራሉ።