From Wikipedia, the free encyclopedia
ጥቅምት ፲፮ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፳ ቀናት በዮሐንስ፤ በማቴዎስ፤ እና በማርቆስ ዘመናት ደግሞ ፫፻፲፱ ቀናት ይቀራሉ
፲፱፻፵፬ ዓ.ም በብሪታንያ ብሔራዊ ምርጫ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር በነበሩት በዊንስተን ቸርቺል የሚመራው የኮንሰርቫቲቨ ፖለቲካ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቸርቺልም ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ።
፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ቦይንግ 707 አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ ከኒው ዮርክ ከተማ ተነስቶ በፈረንሳይ አገር ፓሪስ ከተማ ድረስ በረረ።
፲፱፻፷ ዓ.ም ለ ሀያ ስድስት ዓመት በኢራን አልጋ ላይ ከተቀመጡ በኋላ ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ በራሳቸው እጅ ዘውድ ጫኑ። የሚስታቸውን የንግሥት ፋራንም ዘውድ ጫኑላቸው።
፲፱፻፸፪ ዓ.ም የደቡብ ኮሪያው የጸጥታ ኃላፊ ኪም ጄ ክዩ ባልታሰበ አደጋ ፕሬዚደንታቸውን ፓርክ ቹንግ ሂን በሽጉጥ ገደሉ።
፲፱፻፹፯ ዓ.ም የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን በተገኙበት ስርዐት ዮርዳኖስ እና እስራኤል የዕርቅ ስምምነት ተፈራረሙ።
፲፱፻፺፬ ዓ.ም ብዙ ተችዎች በኢትዮጵያ በ ፳፻፩ ዓ.ም የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ መንግሥት ያጸደቀውን “ጸረ ሽብር” ሕግ ምሳሌ ሆኖለታል የሚባለው የአሜሪካው “ፔትርዮትስ አክት” (Patriots Act) ህግ ሆኖ ጸደቀ።
፲፱፻፲፪ ዓ.ም የመጨረሻው የኢራን ንጉሠ ነገሥት ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ
፲፱፻፵ ዓ.ም የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ሚስትና ስድሳ ሰባተኛዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂላሪ ሮዳም ክሊንተን
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.