ጥር ፲፩
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጥር ፲፩ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፴፩ ኛው ዕለት ሲሆን ፲፮ ኛው የበጋ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፪፻፴፭ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፪፻፴፬ ዕለታት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በመጥምቁ ዮሐንስእጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ የጥምቀት በዓል ነው።