ጠላ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጠላየኢትዮጵያ ባህላዊ መጠጥ ነው። ይህ መጠጥ ከገብስና ከጌሾ ተጠንስሶ የማሽላ፣ ዘንጋዳ፣ የጤፍ፣ የሰንዴ ወይም የዳጉሣ ቂጣ (እንኩሮ)በመጨመር የሚሠራ ሲሆን ከ2%-4% አልኮሆል ይዘት አለው። ጠላ ከተጠመቀ በኋላ በ3 ቀን ውስጥ ለመጠጣት ይደርሳል። ሆኖም ተደፍድፎ በቆየ ቁጥር እየበሰለና እየበረታ ስለሚሄድ ማቆየቱ ይመረጣል። በዚህም ምክንያት አፍለኛና ጥሩ የሚባሉ ደረጃዎች አሉት። ከዋናው የጠላ አይነት በተጨማሪ ሌሎች ሁለት አይነት ጠላዎች አሉ፣ እነርሱም
- ቡቅሪ -- አልኮሆል የሌለው
- ፊልተር ጠላ --- (6% አልኮሆል)