ዠመዱ ማርያም
From Wikipedia, the free encyclopedia
ዠመዱ ማርያም በምስራቅ ላስታ፣ ከአላማጣ 10ማይል በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኝ፣ ዋሻ ዋስጥ የሚገኝ፣ መስቀል ቅርጽ ያለው ቤተ ክርስቲያን ነው። ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ይሄን ቤተክርስቲያ በ1510ቹ ሲጎበኝ፣ በዘመኑ ብዙ ቀሳውስትና መነኮሳት በቤተክርስቲያኑ ስር ይተዳደሩ እንደነበር ይጠቅሳል። መኖሪያቸውም ከዋሻው ውጭ በተራራው ላይ እንደነበርና መነኮሳት ከዋሻው ስር፣ ቀሳውስት ደግሞ ከዋሻው በላይ ይኖሩ እንደነበር ይናገራል[1]። በዚህ ዘመን ቤተርክርስቲያኑ ይኩኖ አምላክ ማርያም ይባል እንደነበር ይዘግባል[2]።
Quick Facts ከአለት የተፈለፈለ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን, ዠመዱ ማርያም ...
| ||||
---|---|---|---|---|
ዠመዱ ማርያም | ||||
[[ስዕል: | ||||
ዠመዱ ማርያም | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ሌላ ስም | ይኩኖ አምላክ ማርያም (በ15ኛው ምዕተ ዓመት) | |||
ዓይነት | ዋሻ ውስጥ የሚገኝ ቤ.ክ. | |||
አካባቢ** | ||||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን | ||||
* የአለበት ቦታ ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |
Close
ጀመዱ ማርያም፣ በልዩ አወቃቀሩ (ለምሳሌ ብዙ ቅስቶችን በመጠቀም፣ በትክክል በተቀረጹ ቀይ የደንጊያ ግድግዳዎቹ፣ መስቀል ቅርጽ በመያዙ) እና በግድግዳው ውጭ ላይ በተሳሉት ልዩ ልዩ ምስሎቹ ይታወቃል። አሰራሩም ከተራራ ስር ሲሆን አንድ ጠባብ መግቢያ ብቻ ያለውና ለማያውቅ ሰው በሩ የት እንደሆነ የማይታወቅ ቤ/ክርስቲያን ነው[3]።