የፎሪየር ሽግግር
From Wikipedia, the free encyclopedia
From Wikipedia, the free encyclopedia
የፎሪየር ሽግግር አንድን የአቅጣጫ ቁጥር ፈንክሽን ወደ ሌላ አቅጣጫ ቁጥርፈንክሽን ይሚያሻግር የሂሳብ መሳሪያ ነው። በተለይ በሲግናል ዝግጅት ጥናት ፣ የመጀመሪያው ፈንክሽን ግቤት ጊዜ ሲሆን የጊዜ ግዛት ውስጥ ያለ ፈንክሽን ያስብለዋል። የፎሪየር ሽግግሩ እንግዲህ ይህን በጊዜ ግዛት ውስጥ ያለ ፈንክሽን ወደ ድግግሞሽ ግዛት ውስጥ ወዳለ ፈንክሽን በማሻገር አዲሱ ፈንክሽን ግቤቱ ድግግሞሽ እንዲሆን ያደርጋል። አዲሱ ፈንክሽን የቀደሞው ፈንክሽን የድግግሞሽ ተወካዩ ይባላል። ይህ እንግዲህ ውሃ-ቅዳ-ውሃ-መልስ ሊመስል ይችላል ሆኖም ግን በተግባር ሲታይ እጅግ ጠቃሚና ለብዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መሰረታዊ ጠቀሜታ ያመጣ ነው (ለምሳሌ የጅ ስልክወን ሲያነሱ በስልክወ የሚያዳምጡት የሌላውን ሰው ድምጽ ሳይሆን የድምጹን ፎሪየር ሽግግር ነው)።
በፎሪየር ሽግግር የመጣው አዲሱ ፈንክሽን ቀደሞ በጊዜ ግዛት በነበረው ፈንክሽን ውስጥ ተሸሽገው የነበሩትን የድግግሞሽ መጠኖች ይፋ ያወጣል።
ብዙ አይነት የሂሳብ ትርጉሞች ቢኖሩም፣ ቀላሉና ለምህንድስና የሚያገለግለው ትርጉም በዚህ መልኩ ይቀመጣል፦
እዚህ ላይ x ጊዜን ሲወክል ፣ የተሻገረው ተለዋጭ ξ ደግሞ ድግግሞሽን ይወካላል። ሁልጊዜም ባይሆን፣ በጊዜ ግዛት ያለውን ƒ በአመቺ ጊዜ መልሰን ከድግግሞሽ ግዛት ካለው ማግኘት እንቻላለን፣ በዚህ መልኩ
ይህ እንግዲህ ተገልባጭ የፎሪየር ሽግግር ይሰኛል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
~
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.