የዮሐንስ ራዕይመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን መጨረሻ ይገኛል። ይህ የመፅሃፉ ክፍል በክርስቲያኖች የአለም ፍፃሜ ጥናት ውስጥ ዋና ሚና አለው። የተፃፈው በኮይኔ ግሪክ ሲሆን አርዕስቱ አፖካሊፕሲስ ነው። ትርጉሙም መግለጽ ወይም ማሳየት ማለት ነው። ፀሃፊው ራሱን በፅሁፉ ውስት ዮሃንስ ብሎ ያሳወቀ ሲሆን ፍጥሞ የምትባል በኤጊያን ባህር የምትገኝ ደሴት ላይ እንደነበር ታላቅ ድምፅ እንደሰማና ፅሁፉንም እንዲፅፍ እንደታዘዘ ይገልፃል። ይህኛው ዮሃንስ በውርስ መሆን ያለበት ሐዋርያው ዮሃንስን ቢሆንም አዳዲስ ጥናቶች የተለያዩ ምልከታዎችን ይሰነዝራሉ ከነኝህ ውስጥም ሌላ የፍጥሞ ዮሃንስ የሚባል ሰው እንደነበር ይገልጻሉ። ብዙ አዳዲስ አጥኝዎች ፅሁፉ የተፃፈው በ95 አ.ም ነው ሲሉ አንዳንዶች ግን በ70 አ.ም ነበር ብለው ይገምታሉ። በዚህ ራዕይ ወይም ትርዒት ስለዚሁ አለም መጨረሻው ቀን ትንቢት በሕልሙ ያቀርባል።

መፅሀፉ በሦስት ክፍል ይዋቀራል። የመጀመሪያው የማስታወሻዎች ሲሆን ሁለተኛው የፍፃሜውና ሦስተኛው የትንቢት መልእክቶች ናቸው።

[ዩሀንስ ስናገር በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ ይላል። የጌታ ቀን ሰንበት ነበር። ይሀዉም ቅዳሜ ነዉ።]

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.