የአንድ ፍቅር ሰላም ትዕይንት

From Wikipedia, the free encyclopedia

የአንድ ፍቅር ሰላም ትዕየንት (እንግሊዝኛ፦ One Love Peace Concert) በሚያዝያ 14 ቀን 1970 ዓም በኪንግስተን ጃማይካ የተከሠተ ሬጌ ሙዚቃዊ ትርዒት ነበረ።

በዚሁ ወቅት በጃማይካ በፖለቲካዊ ፓርቲዎቹ መካከል የእርስ በርስ ጦርነት ያህል ኹኔታ ነበረ። እነኚህ ፓርቲዎች የጃማይካ ሠራተኞች ፓርቲ (JLP) እና የጃማይካ ሕዝቦች ብሔራዊ ፓርቲ (PNP) የተባሉ ሲሆን፣ በትዕይንቱ ከፍታ ቦብ ማርሊ እና ቡድኑ ዘ ዌይለርስ ዘፈኑን «ጃምን» እያጫወቱ፣ ማርሊ ሁለቱን ተቃራኒ የፓርቲ መሪዎች ማይከል ማንሊ (የዛኔ ጠቅላይ ሚኒስትር) እና ኤድዋርድ ሲያጋ ከተመልካቾች መሃል ወደ መድረክ ጠርቶ እጅ በእጅ አስተባበራቸው። ይህም ዝነኛ ድርጊት በፊልም በመቀረጹ አሁንም ብዙ ጊዜ ታይተዋል።

የኮንሰርቱ ምክንያት የጃማይካ ፖለቲካዊ ጦርነት ሁኔታ ለማረጋጋት ነበር። በኮንሰርቱ 32,000 ተመልካቾች መጡ። ከነቦብ ማርሊ 16 የጃማይካ ሬጌ ሙዚቃ ቡድኖች ወይም ዘፋኞች ተሰሙ።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.