ዘቅዱስ ሕርያቆስ From Wikipedia, the free encyclopedia
፻፳፬ ፤ ለጸሎት ተነሡ አቤቱ ይቅርበለን ሰላም ለሁላቹህ ይሁን
ከመንፈስህ ጋራ ።
፻፳፭ ፤ የመፈተት ጸሎት ።
ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የጀመረ ሁሉንም የፈፀመ ሁሉንም የጨበጠ እግዚአብሔር መላዕክትና የመላዕክት አለቆች መናብርትና ሥልጣናት አጋእዝትና ኃይላት ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትም ድርገታትም የሚሰግዱለት ተገዢዎችና ግዛቱ ጉልቱም ናቸውና በሁሉ ባለጠጋ ሲሆን ራሱን ከሁሉ ድሀ አደረገ ።
፻፳፮ ፤ ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከሞትም አደረሰው ።
፻፳፯ ፤ የሚስቡትን ሰዎች በቀንዱ የማይበረታታ ለሚያርዱትም ሰዎች አንገቱን የሚያዘነብል ላም ምን ይደንቅ ።
፻፳፰ ፤ በሚሸልተው ፊት የማይናገር በግ እንደምን ያለ ነው ?። በመከራው ጊዜ በሚወጉት ፊት አፉን ያልገለፀ ምን ትዕግሥት ነው ?።
፻፳፱ ፤ ዮሴፍ ከተወጃጃት ክቡር ዕንቁም በውስጧ ካገኘባት ሣጥን የተገኘ ኅብስት እንደምን ያለ ነው?።
፻፴ ፤ በውስጧ ሰው ካልገባባት አዳራሽ የተገኘ ጽዋ እንደምን ያለ ነው ?።
፻፴፩ ፤ ፈፅሞ የተለየ ሳይሆን ከዚህ ኅብስት የተለየ ይህ ትእምርተ መስቀል ምን ድንቅ ነው መልኩ ልምላሜው ጣዕሙ አንድ ነው እንጂ ።
፻፴፪ ፤ መለኮቱ ከሰውነቱ ፈፅሞ የተለየ እንዳይደለ እንደዚሁም ይህ ትእምርተ መስቀል ከዚህ ኅብስት ፈፅሞ የተለየ አይደለም ።
፻፴፫ ፤ እንዲሁም ገናናነትህ ከትሕትናችን ትሕትናችን ከገናናነትህ ጋራ አንድ ይሁን ዓለምን የያዝህ አንተ አምላካችን ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.