![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/1/17/%25E1%258A%25A5%25E1%2588%2598%25E1%2589%25A5%25E1%2588%25AD%25E1%2588%2583%25E1%258A%2595.png/640px-%25E1%258A%25A5%25E1%2588%2598%25E1%2589%25A5%25E1%2588%25AD%25E1%2588%2583%25E1%258A%2595.png&w=640&q=50)
የማርያም ቅዳሴ
ዘቅዱስ ሕርያቆስ / From Wikipedia, the free encyclopedia
አባ ሕርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ አምላክን ስለ ወለደች ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ የደረሰው የቁርባን ምስጋና ይህ ነው ። ልመናዋ በረከትዋ ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን ።
Quick Facts የማርያም ቅዳሴ ዘቅዱስ ሕርያቆስ, የቅዱስ ሕርያቆስ የንግሥ ቀን ...
የማርያም ቅዳሴ![]() | |
---|---|
የቅዱስ ሕርያቆስ የንግሥ ቀን | ጥቅምት ፪ (ያረፈበት) |
የትውልድ ሀገሩ | ግብፅ (ብኅንሳ) |
የተወለደበት ዘመን | ዘመነ ሊቃውንት (ከ፫፻ እስከ፬፻ ዓ.ም) ማለት ነው |
Close
፩ ፤ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ። ከመንፈስህ ጋር አምላካችንን አመስግኑት ። እውነት ነው ይገባዋል ። ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ ። በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ አለን ።
፪ ፤ ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ ።ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ ። ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ ።
፫ ፤ እኔም የማርያምን ቅዳሴ እናገራለሁ ። በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ ። እኔም የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ ። መዘንጋት ባለበት ቃል በማስረዘም አይደለም ። በማሳጠር ነው እንጂ እኔም የድንግልን ገናንነትዋን እናገራለሁ ።
፬ ፤ ዛሬ በዚች ቀን በፍቅርና በትሕትና ግሩም በሚሆን ምሥጢር ፊት እቆማለሁ ። በዚህ ማዕድና ቁርባን ፊት ።
፭ ፤ መንፈሳቸውን ያረከሱ ሰዎች ከርሱ ሊቀምሱ የማይቻላቸው በእውነት ቁርባን ነው ። በበግ በጊደርና በላም ደም እንደ ነበረው እንደ ቀደሙት አባቶች መሥዋዕት አይደለም እሳት ነው እንጂ ።
፮ ፤ ፈቃዱን ለሚሠሩ ልቦናቸውን ላቀኑ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው ። ስሙን ለሚክዱ ለዓመፀኞች ሰዎች የሚበላ እሳት ነው ።
ገፅ ፩