From Wikipedia, the free encyclopedia
የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ከጥንታዊ ግብጽ የተገኘ ቅርስ ሲሆን፣ ኩልን ወዘተ. ለማደባለቅ ከተጠቀሙት ሠሌዳዎች አንድ ነው። የተሠራበት ዘመን 3100 ዓክልበ. አካባቢ መሆኑ ይታመናል። ይህም በፈርዖኖች ቅድመ-ዘመን ነበረ፤ በአባይ ወንዝ ሸለቆ የነበሩት ሀገራት በአንድ የግብጽ መንግሥት ገና ሳይዋሀዱ ማለት ነው።
በሠሌዳው ፊት ላይ፣ በሦስት መስመሮች የሚራመዱ እንስሶች (ከብት፣ አህያና ፍየል) ይታያሉ። አራተኛውም መስመር አትክልትን ያሳያል። በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ፣ በአትክልቱ አጠገብ አንዱ ምልክት «ቴሄኑ» (ልብያ) የሚባል ሃይሮግሊፍ ነው፤ ስለዚህ ሠሌዳው ደግሞ የቴሄኑ ሠሌዳ ወይም የሊብያ ሠሌዳ ተብሏል። ሌሎች ሊቃውንት ግን ምልክቱ «ቴሄኑ» አይደለምና የግዮን ሸለቆ ከቶሞች ይሆናሉ ብለዋል።
በሠሌዳው ጀርባ ሰባት መንደሮች ወይም ከተሞች አሉ። እነዚህ 7 ከተሞች በግድግዳዎች ውስጥ ሲሆኑ እያንዳንዱ ከተማ በውስጡና በላዩ ልዩ ልዩ ምልክት አለበት። በላዩ ያለው ምልክት መኰትኰቻ የያዘ አውሬ፣ ተኋን ወይም ወፍ አይነት ነው። ከዚህ ጭምር በየከተማው የቅያስ ምልክቶች በልዩ ልዩ መጠኖች አሉ። በድምሩ 28 ቅያሶች አሉ፤ ይህ ምናልባት የሕዝብ ወይም የሕንፃ ብዛት ያመልክታል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.