![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/5/56/%25E1%2588%259A%25E1%258A%2593%25E1%2588%25B5-%25E1%258A%25A1%25E1%2588%25AB%25E1%258A%25AA%25E1%258B%25B3%25E1%258A%2590_%25E1%2588%259D%25E1%2588%2585%25E1%2588%25A8%25E1%2589%25B5.jpg/640px-%25E1%2588%259A%25E1%258A%2593%25E1%2588%25B5-%25E1%258A%25A1%25E1%2588%25AB%25E1%258A%25AA%25E1%258B%25B3%25E1%258A%2590_%25E1%2588%259D%25E1%2588%2585%25E1%2588%25A8%25E1%2589%25B5.jpg&w=640&q=50)
ሚናስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ዓፄ ሚናስ በዙፋን ስማቸው ቀዳማዊ አድማስ ሰገድ ከ1559 እስከ መጋቢት 1፣ 1563 እ.ኤ.አ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የነበሩ መሪ ናቸው። የአጼ ገላውዲዎስ ወንድም ሲሆኑ የአጼ ልብነ ድንግል ልጅም ናቸው።
==
Quick Facts ዓፄ ሚናስ, ግዛት ...
ዓፄ ሚናስ | |
---|---|
![]() | |
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ | |
ግዛት | ከ1559 እስከ 1563 እ.ኤ.አ. |
ቀዳሚ | ዓፄ ገላውዴዎስ |
ተከታይ | ዓፄ ሠርፀ ድንግል |
ባለቤት | እቴጌ አድማስ ሞገሴ |
ሙሉ ስም | ቀዳማዊ አድማስ ሰገድ (ዙፋን ስም) |
ሥርወ-መንግሥት | ሰሎሞን |
አባት | ዓፄ ልብነ ድንግል |
እናት | እቴጌ ሰብለ ወንጌል |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና |
Close
==
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/7/70/Historiademins00este_bw.pdf/page5-640px-Historiademins00este_bw.pdf.jpg)
በአህመድ ግራኝ ጦርነት ዘመን ህጻኑ ሚናስ በምርኮ ተያዘ። ሆኖም ግን ከሌሎች እስረኞች በተለየ መልኩ በግራኝ አህመድ ሚስት በድል ወምበሬ እንደተያዘ ታሪክ ያትታል። በእስር ዘመኑ ሚናስ የባቲ ድልወምበሬን ልጅ አግብቶ ይኖር ነበር። ሆኖም ግራኝ አህመድ በ1542 ከየመን እና መሰል እስላም አገሮች ለሚያደርገው ጦርነት እርዳታ ለማሰባሰብ ሲል ሚናስንንና ሌሎች ውድ ስጦታወችን ለየመኑ ሱልጣን ዘቢድ ፓሻ ላከ [1] ሆኖም ግን በወይናደጋ ጦርነት የግራኝ አህመድ ጦር ሲሸነፍ የግራኝ ልጅ በሚናስ ወንድም በአጼገላውዲወስ ተማረከ። ይህን እስረኛ በመጠቀም ገላውዲወስ ወንድማቸውን ሚናስን ከየመን አገር በእስረኛ ልውውጥ እንዲመጣ አደረጉ። በዚህ ጊዜ በአገሪቱ ለብዙ ቀናት ከፍተኛ ደስታ እንደነበር ታሪክ ተመራማሪ ሪቻርድ ፐንክኽርስት መዝግቧል፡፡[2]